ኢትዮ ቴሌኮም በ2012 በጀት ዓመት 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ።

የድርጅቱ ዋና ስራ አስፈጻሚ ወይዘሪት ፍሬህይወት ታምሩ ዛሬ በተቋሙ የ2012 በጀት ዓመት አፈጻጸም ዙሪያ በሰጡት መግለጫ ድርጅቱ 47 ነጥብ 7 ቢሊዮን ብር ትርፍ አግኝተናል ብለዋል።

ከትርፉ ላይም 11 ነጥብ 3 ቢሊየን ብር ግብር ከፍያለሁ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም 318 ነጥብ 4 ሚሊየን ዶላር እዳንም ከፍያለሁ ብሏል።

እንደ ወ/ት ፍሬህይወት የተገኘው ትርፍ ከአምናው ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር የ31 ነጥብ 4 መቶ ብልጫ አለው ።

በአጠቃላይ የኢትዮ ቴሌኮም ደንበኞች ቁጥር 46.2 ሚሊዮን ደርሷልም ብለዋል።

የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 44.5 ሚሊዮን፣ የዳታ እና የኢንተርኔት ተጠቃሚ 23.8 ሚሊዮን፣ የብሮድባንድ ደንበኞች ብዛት 212.2 ሺ እንዲሁም የመደበኛ ስልክ 980 ሺ ደንበኞች አሉትም ተብሏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 23 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *