በቦሌ አርፖርት ሰባት ስናይፐር ወደ አገር ውስጥ በህገ ወጥ መንገድ ሊገባ ሲል መያዙ ተሰማ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ስናይፐሩ የተያዘው በተበታተነ መልኩ በቦርሳዎች ከሌሎች እቃዎች ጋር ተጠቅልለው እንደነበር ተገልጿል። በቀን 25/12/12 በቦሌ ኤርፖርት አለማቀፍ በረራ መግቢያ በኩል ከሳዑዲ አረብያ የመጣ አንድ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጅዳ ጠቅልለዉ ወደ ሀገራቸዉ እንደሚገቡና የሚይዙት የግል መገልገያ ዕቃ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆንላቸዉ ደብዳቤ መያዛቸው ተገልጿል። ግለሰቡ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ከግል መገልገያ ዕቃዎቻቸዉ ጋር ተገጣጥሞ […]

የመጀመርያው ታሪካዊው የንግድ አይሮፕላን ከእስራኤል ተነስቶ የተባበሩት አረብ ኤምሬት አርፏል።

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ኤል አል አየር መንገድ የአሜሪካንና የእስራኤልን ተወካዮች ይዞ የሶስት ሰአት በረራ በማድረግ የተባበሩት አረብ ኤምሬት መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡ በረራው ለእስራኤል የተከለከለ የነበረውን የሳኡዲ አረቢያ የአየር ክልል እንዲያልፍ ተፈቅዶለታል፡፡ ከተመሰረተችበት እንደ አውሮፓውያኑ 1948 ጀምሮ ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እስራኤልን እንደ ሀገር እውቅና የሰጠቻት የመጀመርያዋ ሀገር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ነች፡፡ ቅዳሜ ነበር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከ 1972 […]

በአዲስ አበባ በአምሰት ክፍለ ከተሞች ብቻ ከ210 ሺህ ካሬ ሜተር በላይ መሬት መወረሩን ኢዜማ አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት በ2012 በጀት ዓመት መስከረም ወር ላይ ለባለዕድለኞች ወጥተዋል ያላቸው ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች መተላለፉንም አስታውቋል። የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በአዲስ አበባ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በሚመለከት ለአንድ ወር አደረኩት ያለውን የጥናት ግኝት ዛሬ ይፋ አድርጓል። እንደ ፓርቲው ጥናት መሰረት ከሆነ በአዲስ […]

የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ጠበቃ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ ደንበኛዬ እየተጉላላብኝ ነው አለ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ከአርቲስት ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ ከቤታቸው የተያዙት ኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ያለ ፍርድ እስር ቤት እንደሚገኙ ነው ጠበቃቸው የተናገሩት፡፡ የኢንጅነር ይልቃል ጌትነት ጠበቃ የሆኑት አቶ አዲሱ ጌታነህ ደንበኛዬ ከተያዘ ሁለት ወር እንደሞላው ተናግረው በነዚህ ሁሉ ጊዜያቶች ውስጥ ፖሊስ ለምርመራ ጊዜ እየወሰደ ፍርድ ቤትም ተገቢ ያለውን ጊዜ እየሰጠ እስካሁን ድረስ ቆይተናል፡፡ ነገር ግን ፖሊስ ምርመራዬን ጨርሻለሁ […]

ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በአምስት መስመሮች ከ3 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር የባቡር ሀዲድ ለመገንባት ማቀዷን አስታወቀች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታ አሁን ካለበት 902 ኪሎ ሜትር ወደ 4ሺ ኪሎ ሜትር ለማድረስ እቅድ ተነድፏል። የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመንና የተጓዦችን ደህንት ከመጠበቅ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፆ ይኖረዋል የተባለለት የ10 ዓመት የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ ኢትዮ ኤፍ ኤምም በ10 ዓመት መሪ እቅዱ መሰረት የካርቦን ልቀትን የሚቀንሰው የኤሌክሪክ የባቡር መስመር ዝርጋታ የት ይደርሳል? ሲል […]

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሰራተኞች ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ ከ17 ሚሊየን ብር በላይ የቦንድ ግዢ እንደሚፈጽሙ አስታወቁ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሚሽኑ አመራርና ሠራተኞች ከ17 ሚሊዮን 327 ሺህ ብር በላይ ለታላቁ የህዳሴ ግድብ ግንባታ የሚውል ቦንድ ለመግዛት ወሳኔ አስተላልፈዋል፡፡ ሰራተኞቹ ከጥቅምት ወር 2013 ዓ..ም ጀምሮ ከደመወዛቸው በሚቆረጥ የአንድ ወር የተጠራ ደመወዛቸውን በ17 ሚሊዮን 327 ሺህ ብር ቦንድ ለመግዛት ነው ውሳኔ ያስተላለፉት፡፡ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽር ጄኔራል ጀማል አባሶ እንዳሉት የኢትዮጵያ መንግስት የመጀመሪያ የውሃ ሙሌትን በተሳካ […]

በጋምቤላ ክልል በጆር ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ከስድስት ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የክልሉ ፕረስ ሴክረታሪያት ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በጆር ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል። የክልሉ ዕርሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በቦታው ድረስ በመገኘት በጎርፉ ምክንያት የተጎዱትን ማህበረሰብ ምልከታ አድርገዋል፡፡ ችግሩን ለመቅረፍ ዘላቂነት ያለው ስራ እየተሰራ መሆኑንም ፕሬዘዳንቱ አስታውቀዋል፡፡ አያይዘውም በአሁን ወቅት ለተጎጂዎች እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ በቂ ያለመሆኑን ገልጸው የሚመለከታቸው አካላቶች ሁሉ ለረባረቡ […]

የሱዳን አማፅያን ለ17 ዓመታት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም ከመንግስት ጋር ተስማሙ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የሱዳን ዋና የአማፅያን ህብረቱ ከመንግስት ጋር ቁልፍ የሰላም ስምምነት ለማከናወን መስማማታቸውን ታዋቂው የዜና ወኪል ሱና ዘግቧል፡፡ የሀገሪቱ መንግስት ከአማፅያኑ ጋር የሰላም ስምምነቱ ታላሚ ያደረገው ለ 17 ዓመት የዘለቀውን ግጭት ለማስቆም መሆኑ ተገልጧል፡፡ የሱዳን አብዮታዊ ግንባር (SRF) ፤ የምዕራብ ዳርፉር ክልል አማፅያን እና በደቡብ ኮርዶፋን ክልል የትጥቅ ትግል የሚያደርጉ ሀይሎች ከመንግስት ጋር የሰላም ስምምነት ለማድረግ ፍቃደኛ […]

ግብፅ በፀረ-ሽብር ዘመቻ 77 አክራሪ ታጣቂዎች መግደሏ አስታወቀች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ግብፅ በ30 ቀናት ውስጥ ባከናወነችው የፀረ-ሽብር ዘመቻ ከ70 በላይ ፅንፈኛ ታጣቂዎችን መገደላቸውን የሀገሪቱ ጦር ሀይል ተናግረዋል፡፡ በዘመቻው መሪዎቻቸውን ጨምሮ 73 አሸባሪዎች የተገደሉት በሰሜናዊ ሲናይ ይኖሩበታል ተብሎ ታላሚ በተደረገ መኖሪያ ቤቶች ላይ በተከናወነ ጥቃት መሆኑን ጦሩ ይፋ አድርጓል፡፡ ፅንፈኛ የግብፅ አክራሪ ታጣቂዎችን ለማፅዳት በተወሰደ እርምጃ 77ቱ መገደላቸውን ያሳወቀው የሀገሪቱ ጦር በጠቅላለው ከ317 በላይ ቤቶች እና ምሽጎች […]

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ለ61 ፖሊስ አባላት የማዕረግ እድገት ሰጠ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በዚህም መሰረት 2 የምክትል ኮሚሽርነት 7 የረዳት ኮሚሽርነት እና ለ52ቱ ደግሞ ከኮማደር እስከ ኢንስፔክተርት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡ የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ኮሚሽር ጄኔራል ጀማል አባሶ እንደተናገሩት የዛሬው ሹመት በፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በማዕረግ ደረጃም ሆነ በብዛት ከፍተኛው ነው፡፡ ከላይ እስከ ታች ያለው የተቋሙ አመራር እና ሰራተኛ ተናቦ በመስራቱ ባለፉት ሁለት ተከታታይ ዓመታት ኮሚሽኑ ውጤታማ መሆኑን […]