ሶስት የጋምቢያ ሚኒስትሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቁ።

እንደ ጋምቢያ ፕሬዝዳንት ፅ/ቤት መግለጫ ሶስት የካቢኔው ሚኒስትሮች በኮቪድ 19 መያዛቸው ተረጋግጧል፡፡

የፋይናንስ ሚኒስትሩ፣ የነዳጅና ኢነርጂ ሚኒስትሩ ፣ የግብርና ሚኒስትሩ በኮሮና መጠቃታቸው ተረጋግጧል፡፡

ፕሬዝዳንት አዳማ ባሮው ባለፈው ሳምንት ምክትል ፕሬዝዳንታቸው ኢሳቱ ቱሬይ በኮሮና መጠቃታቸውን ተከትሎ ራሳቸውን ለይተዋል፡፡

የጋምቢያ መንግስት የፊት መሸፈኛ ማስኮችን ህዝብ በሚሰበሰብባቸው ቦታዎች አስገዳጅ ያደረገ ሲሆን ማንኛውም ማህበራዊ ስብስቦችን እንደከለከለ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በጋምቢያ እስካሁን 498 ሰዎች በኮሮና ሲጠቁ 9 ያህል ደግሞ ህይወታቸው አልፏል፡፡

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.