በኢራን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር መንግስት በይፋ ካሳወቀው ሶስት ዕጥፍ መሆኑን አንድ የምርመራ ዘገባ አረጋገጠ።


በኢራን በኮሮና ምክንያት ህይወታቸው ያለፈው ሰዎች ቁጥር መንግስት በይፋ ካሳወቀው ሶስት ዕጥፍ መሆኑን የቢቢሲ የፐርሺያ አገልግሎት ባደረኩት ምርመራ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

የኢራን መንግስት እንደ አውሮፓውያ እስከ ሀምሌ 2020 ድረስ፤ 42 ሺህ ዜጎቼ በኮሮና ሞተዋል ሲል በሰነድ ያስቀመጠ ሲሆን በጤና ሚኒስቴሩ በኩል በይፋ የተናገረው ግን 14 ሺህ 405 ሰው እንደሞተ ነው፡፡

በኮቪድ 19 የተጠቃው ሰው ብዛትም በይፋ ከተነገረው እጥፍ ነው ተብሏል፡፡ በትክክል የተጠቃው 451 ሺህ 24 ሲሆን በይፋ የተነገረው ግን 278 ሺህ 827 ነው፡፡

በመንግስት በይፋ የተነገረው ቁጥር ራሱ ኢራንን በመካከለኛው ምስራቅ በቫይረሱ ክፉኛ የተጠቃች ሀገር ያደርጋታል፡፡

ከቅርብ ሳምንታት ወዲህ ደግሞ ስርጭቱ በድጋሚ ከፍ እያለ መጥቷል፡፡

ለቢቢሲ በተላኩ የህክምና ሰነዶች መሰረት የመጀመርያው ሞት በኢራን የተከሰተው እንደ አውሮፓውያኑ ጥር 22 2020 ነው፡፡

ይሄ ደግሞ በይፋ የመጀመርያው ሞት ተከሰተ ተብሎ በመንግስት ከተነገረበት 1 ወር በፊት ነው፡፡

ኮሮና በኢራን ከገባ ጀምሮ በይፋ የሚነገሩት ቁጥሮች ላይ ከፍተኛ ጥርጣሬ እንደነበር ቢቢሲ የዘገበ ሲሆን በብሔራዊና በክልል ደረጃ የሚነገሩት ቁጥሮች ላይ መጣረስ ነበር ብሏል፡፡

በሔኖክ አስራት
ሐምሌ 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.