አሜሪካ በመጪዎቹ ቀናት የቻይና ሶፍትዌሮችን ከአገራቸው እንደምታስወገድ አስታወቀች።


የአሜሪካው ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ነው ብለው በሚያምኑት በቻይና ባለቤትነት በተያዙ የሶፍትዌር መተግበሪያዎች ላይ በመጪው ቀናት እርምጃ አንደሚወስዱ የውጭ ጉዳይ ሚንስትሩ ማይክ ፖምፒዮ ተናግረዋል፡፡
ማይክ ፖምፒዮ በንግግራቸውም እንዳሉት ታዋቂው የቪዲዮ መተግበሪያ ቲክ ቶክ ለቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ መረጃ በቀጥታ ከሚመገቡ መካከል አንዱና ዋነኛው ነው ሲሉ ገልፀዋል፡፡
ሚንስትሩ ይህን መሰል አስተያየት ሲሰጡ የተደመጠው ፕሬዘዳንት ትራምፕ ቲክ ቶክ የተባለው የቪዲዮ መተግበሪያ በአሜሪካ አገልግሎት እንዳይሰጥ አግዳለሁ ማለታቸውን ተከትሎ ነው፡፡
ኩባንያው በበኩሉ ቲክ ቶክ በቻይና መንግስት ቁጥጥር ይደረግበታል ፤ መረጃዎችንም ለቤጂንግ ያጋራል በማለት የተሰነዘረውን ክስ ውድቅ አድርጓል፡፡
ፖምፒዮ ዛሬ በፎክስ ኒውስ ቻናል በኩል በሰጡት ቃለ መጠይቅ እንደተናገሩት ሶፍትዌሩ ከቻይና ኮሚኒስት ፓርቲ ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት ያለው በመሆኑ የሚደርሰውን የብሔራዊ ደህንነት ስጋት ግምት ውስጥ በማስገባት እርምጃ ይወሰዳል ብለዋል።
የአሜሪካ እና ቻይና ወዳጅነት አሁን ላይ አስከፊ በሚባል ደረጃ ላይ ያለ ሲሆን ወደ አገራቸው በሚገቡ ምርቶች ላይ ልዩ ቀረጥ ከመጣል አልፎ የዲፕሎማሲ ስራዎች ማሳለጫ ተቋሞቻቸውንም በመዝጋት ላይ ይገኛሉ።

የሁለቱ አገራት ግንኙነት እየተበላሸ የመጣው ዶናልድ ትራምፕ ወደ ስልጣን ከመጡ ጊዜ በኋላ ሲሆን ለግጭቱ ዋነኛ መነሻዎች ደግሞ የጥቅም የበላይነት ለመውሰድ በሚደረግ ጥረት ምክንያት መሆኑን ዘገባዎች ጠቁመዋል።

በሙሉቀን አሰፋ
ሐምል 27 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.