የኮሮና ቫይረስ ስርጭት በአሜሪካ ወደ ሌላ አዲስ ምዕራፍ እንደገባ ተገለፀ።

ኮሮና በልዕለ ሀያሏ ሀገር አሜሪካ ከቁጥጥር ውጪ በሆነ ሁኔታ መሰራጨቱን የቀጠለ ሲሆን አሁን ወደ ገጠሩ የሀገሪቱ ክፍልም በስፋት በመግባት ወደ ሌላ አዲስ ምዕራፍ እንደገባ ተገልጿል፡፡

በነጩ ቤተ መንግስት ለኮሮና ቫይረስ ምላሽ ሰጪ ግብረ ሀይል አስተባባሪ የሆኑት ዶ/ር ዲቦራ ቢሪክስ ለሲኤንኤን እንደተናገሩት ወረርሽኙ በሚያስደነግጥና ከቁጥጥር ውጪ በሆነ መንገድ ተሰራጭቷል ብለዋል፡፡

እስካሁን ከ 4.6 ሚሊዮን በላይ አሜሪካውያን በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ቢያንስ 154 ሺህ 859 ያህሉ ህይወታቸው አልፏል፡፡

እንደ አሜሪካ የበሽታ መከላከልና መቆጣጠር ማዕከል ከሆነ የሟቾች ቁጥር በአሜሪካ ከአንድ ወር በኋላ 173 ሺህ ያህል ይደርሳል ተብሎ ተገምቷል፡፡

እንደ ዶክተሯ ይሄ ነገር በጥብቅ ቁጥጥርና ገደቦች ነው ሊረጋጋ የሚችለው፡፡

ቢያንስ 30 ግዛች በድጋሚ ወደ እንቅስቃሴ የመግባት እቅዳቸውን ለጊዜው ወይ አቁመውታል ወይም አዳዲስ ገደቦችን መጣል ጀምረዋል፡፡

ዶ/ሯ እኔ በጣም የሚያሳዝነኝና የሚያሳስበኝ የቫይረሱን ስርጭት ሳንቆጣጠር በድጋሚ ወደ እንቅስቃሴ ስለመግባትና ት/ቤቶችን ስለመክፈት ማውራታችን ነው ሲሉ ስጋታቸውን አስቀምጠዋል፡፡

በትግስት ዘላለም
ሐምሌ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.