የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 5 ሚሊየን በላይ ቁሳቁሶችን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከ 5 ሚሊየን በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ ቁሳቁሶችን ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች በነገው እለት እንደሚለግስ ለኢትዮ ኤፍ ኤፍ አስታውቋል።

ቁሳቁሶቹ የዩኒፎርም አልባሳት ፤ የህፃናት አልባሳትና መጫወቻዎች እንዲሁም ሌሎች የማብሰያና የመመገቢያ ቁሳቁሶችን ለ 6 መንግስታዊ ላልሆኑ ለጋሽ ድርጅቶች እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ ለዚህ ድጋፍ የሚውል ወደ 17 ኮንቴነር ቁሳቁስ ለተቸገሩ የማህበረሰብ ክፍሎች እንዲደርስ ለመረዳጃ ድርጅቶቹ እንደሚለግስ ተናግሯል፡፡

በደረሰ አማረ
ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.