የሰዎች ለሰዎች የበጎ አድራጎት ማህበር መስራች እና ለበርካታ ኢትዮጵያዊያን ሰብዓዊ ድጋፍ በማድረግ የሚታወቁት ጀርመናዊው ዶክተር ካርል ሄንዝ በስማቸው ፋውንዴሽን ተቋቁሟል።
ፋውንዴሽኑ ዛሬ በአዲስ አበባ የዶክተር ካርል መታሰቢያነት 6 አመት መታሰቢያ ምክንያ በማድረግ ተቋቁሟል፡፡
ዶክተር ካርል ሄንዝ ከ35 አመታት በላይ በተለያዩ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ላይ በመሰማራት በዓለማችን እና በኢትዮጵያ በጎ ስራቸው የሚታወቁ ባለውላታ ናቸው፡፡
ለኒህ ባለውለታ ደማቅ የመታሰቢያ ፕሮግራም ለማድረግ የተቀደ ቢሆንም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ማድረግ እንዳልተቻለ የዶክተር ካርል ቤተሰቦች እና ደጋፊዎች ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታውቀዋል።
በመታሰቢያ ፕሮግራሙ ላይም ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ፣ የተለያዩ ሀገራት ኢምባሲዎች ተገኝተዋል፡፡
ለመታሰቢያ እና ገቢ ለማግኛ በእያመቱ የሚካሄደው የእግር ኳስ እና የሩጫ ውድድር በተጨማሪ በስማቸው የተዘጋጀ ሲዲና 7330 አጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ መስመር ለለህብረተሰቡ ይፍ ተደርጓል፡፡
ኢትዮጵያዊው ዶክተር ካርል በ86 ዓመታቸው ግንቦት 2006 ዓ.ም ባደረባቸው ህመም ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል።
ዶክተር ካርል ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ከድህነት እንዲወጡ ባበረከቱት አስተዋጽኦ የክብር ዶክትሬት የተሰጣቸው ሲሆን በአዲስ አበባ ብስራተ ገብርኤል አካባቢ በስማቸው አደባባይ ተሰይሞላቸዋል።
በሙሉቀን አሰፋ
ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም











