10 ሚሊዮን አፍጋኒስታዊያን በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸውን አንድ ጥናት አመለከተ።

ከአፍጋኒስታን ህዝብ አንድ ሶስተኛው ወይንም 10 ሚሊዮን ያህሉ በኮሮና ቫይረስ ሳይያዝ እንዳልቀረ የአገሪቱ ጤና ሚኒስትር ለናሙና የተሰራ ጥናትን መሰረት አድርገው አስታውቀዋል፡፡

የዳሰሳ ጥናቱ ውጤት የተገኘው በዓለም ጤና ድርጅትና በጆንስ ሆፕኪንስ ድጋፍ፣ በመላ አገሪቱ ከሚገኙ 9 ሺህ 500 ሰዎች ላይ በተደረገ የአንቲቦዲ ምርመራ ነው ሲል አናዱሉ የዜና ኤጂንሲ ዘግቧል።

የጤና ሚነስትሩ አህመድ ጃዋድ ኦስማኒ ቫይረሱ እንዳለባቸው የተረጋገጡ ሰዎች የተገኙት በከተሞች ሲሆን ይህ ደግሞ በዋና ከተማዋ ካቡል የባሰ መሆኑን ገልፀዋል።

አብዛኛዎቹ ግለሰቦች ምልክት የማያሳዩ እንደሆነም ጨምረው ገልፀዋል።

በአፍጋኒስታን 36 ሺህ ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው በምርመራ ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 1 ሺህ 200 ሰዎች ደግሞ ሞተዋል።

አፍጋኒስታን በከፋ ድህነት ውስጥ ስትሆን የጤና ተቋማቷም ለአስርት ዓመታት በዘለቀው ግጭት የተነሳ ወድሟል።

በያይኔ አበባ ሻምበል
ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *