የአነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፍክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍን በቀጣይ 10 አመት የሀገሪቱን 17 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ እዲኖረው እቅድ ተይዟል ተባለ።

በኢትዮጵያ የአነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፍክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍ በቀጣይ 10 አመት የሀገሪቱን 17 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ እንድሚይዝ መታቀዱን ንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ገልጿል ።

የንግድና እና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር አቶ መላኩ አለበል እንደገለጹት ፣ አነስተኛ እና መካከለኛ ማኑፍክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት ዘርፍን አሁን ካለበት 6 ነጥብ 6 በመቶ የኢኮኖሚ ድርሻ በ2022 ወደ 17 በመቶ ለማድረስ እቅድ ይዘናል ብለዋል ።

ባለፉት አመታት ዘርፉን የስራ ዕድል መፍጠሪያ ብቻ አድርጎ መመልከቱ በተያዘው እቅድ ልክ ወደ ኢንድስትሪ መሸጋገር አለመቻሉን አቶ መላኩ ተናግረዋል ።

ጥቃቅን የስራ መስኮችን በሂደት ወደ መካከለኛ ፣ መካከለኛን የስራ መስኮችን ደግሞ ወደ ከፍተኛ መለውጥ ያስፈልጋል ፣ በመሆኑም የዘርፉን ሀገራዊ ጠቀሜታ በመረዳት የሚመለከተው ሁሉ ለውጥ አምጪ ስራ መስራት ያስፈልገዋ ተብሏል ።

በዘርፉ በተደጋጋሚ ከሚነሱ ችግሮች አንዱ የሐይል አቅርቦት ችግር ነው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ደግሞ የህዳሴ ግድቡ የሐይል አቅርቦት ሊፈታው እንደሚችል አቶ መላኩ ገልጸዋል።

ከፌዴራል መስሪያ ቤት ፣ ከክልሎች እና ከሁለቱ ከተማ መስተዳደሮች ተሳታፊዎች በተገኙበት በአነስተኛ እና መካከለኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ዘርፍ ላይ ያሉ ችግሮችን ለመፍታት ያለመ ውይይት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው ።

ዳንኤል መላኩ
ነሀሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *