የፌስ ቡክ መስራች ማርክ-ዙከርበርግ አጠቃላይ ሃብቴ 100 ቢሊዮን ዶላር ደርሷል አለ፡፡

የቴክኖሎጂ ኩባንያ ባለቤቱ ይህን ያለዉ የኩባንያዉ ሸር ሽያጭ በትናንትናዉ እለት በ 6 በመቶ መጨመሩን ተከትሎ ነዉ ተብሏል፡፡
የፌስ ቡክ ኩባንያ መስራቹ ቢሊየነር አሁን ላይ ከፍተኛ ዉዝግብ ከተነሳበት የቻይናዉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ ቲክ ቶክ ጋርም በኢንስታግራም በኩል በትብብር ሲሰራ ነበር የቆየዉ፡፡

ይህም በቴሌግራም በኩል የሚያገኘዉ ገቢም ከፍ እንዲል እንዳደረገለት ቢቢሲ ጽፏል፡፡ወጣቱ ቢሊየነር አሁን ከሃገሩ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ባለቤቶች የማይክሮሶፍት መስራች ቢል ጌትና የኦላይን መገበያያ ኩባንያ አማዞን መስራች ጀፍ ቤዞስ/ Jeff Bezos/ ጋር አድርጓል፡፡

እንደ ብሉምበርግ ዘገባ ደግሞ የኮሮና ቫይረስ መከሰት ለቴክኖሎጂ ኩባንያዎች መልካም እድልን ነዉ ይዞ የመጣዉ፡፡ኩባንያዎቹ ለመዝናኛም ሆነ ለግብይት መፈጸሚያ ቀዳሚ ተመራጭ ሆነዉ እያገለገሉ ይገኛሉ፡፡በዚህም ማርክ ዙከርበርግ በዚህ ዓመት ብቻ 22 ቢሊዮን ዶላር ገቢ ሲያገኝ፤የአማዞኑ መስራች ደግሞ ገቢዉ በ75 ቢሊዮን ዶላር ጨምሯል፡፡

የአሜሪካ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሚባሉት አፕል፣አማዞን፣አልፋቤት፣ፌስቡክና ማይክሮሶፍት የአማሪካን አመታዊ ጠቅላላ ምርት/GDP 30 በመቶ የሚይዙ ናቸዉ ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 1 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *