በቤሩት የደረሰውን ፍንዳታ ተከትሎ ሁለት የሀገሪቱ ሚንስትሮች በገዛ ፍቃዳቸው ስልጣን መልቀቃቸውን አስታወቁ፡፡

በቤሩት ወደብ ወደብ አቅራቢያ ላይ በደረሰው ፍንዳታ ሳቢያ በጥቂቱ ከ158 በላይ ዜጎች ሲሞቱ 6 ሺህ የሚሆኑት ቀላልና ከባድ ጉዳት አስተናግደዋል፡፡

በዚህም ሳቢያ በከተማዋ ሀይል የቀላቀለ የተቃውሞ ሰልፍ በሁለተኛ ቀኑም ቀጥሎ ተስተውሏል፡፡

ከፍንዳታው በኋላ በፈረንሳይና በአሜሪካ የሚመራው አለም አቀፍ ድጋፍ ጥሪ ስብሰባ ተካሂዷል፡፡

በዚህም 300 ሚሊዮን ዶላር ገደማ የሚሆን ገንዘብ ለሊባኖስ ህዝብ በቀጥታ እንደሚሰጥ ቃል ተገብቷል፡፡

በዚህ ውይይት ላይ የነበሩ ሁለት የሀገሪቱ ሚንስትሮች በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣን መነሳታቸውን ገልፀዋል፡፡

ሚንስትሮቹ ስልጣን የለቀቁት በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ለሁለተኛ ጊዜ በጎዳናዎች ላይ በመዘዋወር ጠንካራ ተቃውሞ መቀስቀሱን ተከትሎ ነው፡፡

የሊባኖስ የኢንፎርሜሽን ሚንስትሩ ማናል አብደል ሳማድ ስልጣን መልቀቃቸውን ባሳወቁ በሰዓታት ልዩነት የአካባቢ ጥበቃ ሚንስትሩ ዳሚያኖስ ካታር ስልጣን መልቀቃቸውን ገልፀዋል፡፡

ሚንስትሮቹ ስልጣን መልቀቃቸውን ባሳወቁት ወቅት የሀሰን ዲያብ መንግስት የህዝብን ፍልጎት ማረጋገጥ እንዳልቻለ ተናግረዋል፡፡

በደረሰ አማረ
ነሀሴ 4 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *