የሌባኖስ ፕሬዝደንት የሀገሪቱ መንግስት ያቀረበውን የስራ መልቀቂያ ተቀበሉ፡፡

ባሳለፍነው ማክሰኞ በዋና ከተማዋ ቤይሩት ውስጥ ከደረሰው ፍንዳታ ጋር በተያያዘ የሊባኖስ መንግሥት በገዛ ፈቃዱ ሥልጣን መልቀቁን ትላንት አስታውቋል፡፡

ከ200 በላይ ሰዎች ለሞት የተዳረጉበት ፍንዳታን ተከትሎ ፀረ-መንግሥት ተቃውሞዎች በሀገሪቱ ተቀጣጥሏል፡፡

በርካታ ሊባኖሳዊያን ለፍንዳታው የገዢው ፓርቲ አመራሮችን ይወቅሳሉ፤ በሙስና ተዘፍቀዋል ሲሉ ይከሷቸዋል።

ትላንት ምሽት ላይ ገዢው የሊባኖስ መንግሥት ሥልጣን መልቀቁን በቴሌቪዥን ቀርበው ያሳወቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ሃሰን ዲያብ ናቸው።

ፕሬዝዳንት ሚካኤል አውን ትላንት የጠቅላይ ሚኒስትሩን መልቀቂያ ተቀብለው አዲስ ካቢኔ እስኪመሰረት ድረስ መንግስት በኃላፊነት ላይ እንዲቆይ ጠይቀዋል፡፡

ቤይሩትን ያናወጠው ፍንዳታ የተከሰተው 2750 ቶን የሚመዝን አሞኒዬም ናይትሬት የተባለ ንጥረ ነገር ጥንቃቄ በጎደለው መንገድ ለበርካታ ዓመታት በመከማቸቱ ነው።

ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ በደረሰው ፍንዳታ ምክንያት የሞቱ ሰዎች ቁጥር 220 የደረሰ ሲሆን 110 ሰዎች ደግሞ የገቡበት እንደማይታወቅ የቤይሩት ከተማ ከንቲባ ማርዋን አቡድ አል-ማርሳድ ለተሰኘው የዜና ምንጭ ተናግረዋል።

በያይኔ አበባ ሻምበል
ነሀሴ 5 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.