በደቡብ አፍሪካ ዕለታዊ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር ከ15 ሺህ ወደ 2 ሺህ አሽቆለቆለ።

በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በማይታመን ፍጥነት መቀነሱ ግርምትን ፈጥሯል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሀገሪቱ እለታዊ ሪፖርት 15 ሺህ የነበረ ሲሆን አሁን ግን ይህ ቁጥር ወደ 2 ሺህ 500 ማሽቆልቆሉ ተነግሯል፡፡እንዲሁም ከኮሮና ቫይረስ በተያያዘ የሚከሰተው ሞትም መቀነስ አሳይቷል፡፡

በሀገሪቱ አዳዲስ የወረርሽኙ ተጠቂዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ ቀንሶ ከሰኔ ወር በኃላ ዝቅተኛ ውጤት አግኝታለች፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው የሚያገግሙ ሰዎች መጠን በአማካኝ 62 በመቶ ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ግን 75 በመቶዎቹ አገግመዋል።

ይሁንና ከአፍሪካ ቫይረሱ በፍጥነት ከሚሰራጭባቸው አገራት መካከል ቀዳሚ በሆነችው ደቡብ አፍሪካ ይህ ለውጥ እንደተመዘገበ ዘገባው ያለው ነገር የለም።

በዚህ መክንያትም በደቡብ አፍሪቃ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ተጥሉ የነበረው የእንቅስቃሴ ገደብ እንዲላላና ዝግ ሆነው የከረሙት የንግድ ስፍራዎች እንዲከፈቱ በመንግስት ላይ ግፊት እየተደረገ ነው፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 6 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.