ሞዛምቢክ በቤሩት ከቀናት በፊት ለደረሰው ከባድ ፍንዳታ ኃላፊነቱን አልወስድም አለች።

የሞዛምቢክ መንግሥት በዚህ ወር መጀመሪያ ላይ በሊባኖስ ከፍተኛ ፍንዳታ ያስከተለው የአሞኒየም ናይትሬት ወደ ሞዛምቢክ እየሄደ ያለ እንደነበር ለጋዜጠኞች አረጋግጠዋል፡፡

ምክትል የፍትህ ሚኒስትሩፊሊያሞ ሱዋዚ ኬሚካሉ ወደ ሞዛምቢክ እንዲመጣ የታሰበ መሆኑን አረጋግጠዋል ፡፡

ይሁን እንጂ በዛ ለደረሰው ውድመት ሀገራችን ተጠያቂ አይደለችም ሲሉ መደመጣቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ከዚህ ይልቅ ለጥፋቱ የቤሩት የወደብ ባለስልጣናት ላይ ጣታቸውን ጠቆመዋል ፡፡
መርከቡ ፣ መስከረም 2013 መጨረሻ ላይ ነው ከጆርጂያ ወደ ሞዛምቢክ ቤራ እየተንቀሳቀሰ የነበረው፡፡

ኬሚካሉን የጫነው ድርጅት ሩስታቪ አዞት (Rustavi Azot LLC) የተባለ አሞኒየም ናይትሬት አቅራቢ ነው።

ይህ ኩባንያ አሞኒየም ናይትሬቱን ለኢንተርናሽናል ባንክ ኦፍ ሞዛምቢክ ነው ተቀባይ ብሉ የመዘገበው፡፡

ከዚያም የሞዛምቢክ ባንክ ወኪል ሆኖ ዕቃውን የሚቀበልለት ድርጅት ደግሞ አንድ ትንሽ የሞዛምቢክ ፈንጂ አምራች ኩባንያ ነው።

የዚህ ኩባንያ ሥራ ሌላ ሳይሆን ተቀጣጣይ ፈንጂዎችን ማምረት ነው።

በአግባቡ አልተቀመጠም በተባለው በዚህ ተቀጣጣይ ነገር በደረሰ ፍንዳታከ ከ200 በላይ ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ከስድስት ሺህ በላይ ጎዳት ደርሶባቸዋል፡፡

በዚህ ፍንዳታ ምክንያት በአጠቃላይ 15 ቢሊየን ንብረት ወድሟል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 7 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *