በኢትዮጵያ የእስራዔል ኤምባሲ ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ አበረከተ፡፡

ከስራቸው ባህሪ አንፃር ለኮቪድ 19 ወረርሽኝ ተጋላጭ ከሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች መካከል አንዱ ፖሊስ መሆኑ የሚታወቅ ሲሆን የእስራዔል ኤምባሲ ከ1.5 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመቱ የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብሎች፣ የእጅ ማጽጃ ሳኒታይዘሮች፣ ጓንቶችና የሙቀት መለኪያ መሳሪያዎችን ጨምሮ ሌሎች የህክምና እና የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከያ ቁሳቁሶችን ለኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ በትናንትናው ዕለት ድጋፍ ማድረጉን የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ያደረሰን መረጃ ያስረዳል።

በፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጁ ተገኘተው ድጋፉን ያበረከቱት በኢትዮጵያ የእስራዔል አምባሳደር ራፋኤል ሞራቮ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር የተጠናከረ ግንኙነት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

ፖሊስ ከስራው ባህረ አንጻር ለኮሮና ቫይረስ በከፍተኛ ሁኔታ ተጋላጭ ከሆኑት የህብረተሰብ ከፍሎች አንዱ መሆኑን የገለጹት አምባሳደር ራፋኤል ሞራቮ የእስራዔል ኤምባሲ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ያበረከተው የህክምና ግብዓቶቹ፣ ህግ አስፈጻሚዎች ራሳቸውን፣ቤተሰቦቻቸውን እና ህብረተሰቡን ከወረርሽኙ እንዲከላከሉ ይረዳቸዋል ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ ፕሬዝዳንት ምክትል ኮሚሽነር ጄነራል መስፍን አበበ፣ የእስራኤል ኤምባሲ ለፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ላበረከተው የቁሳቁስ ድጋፍ ምስጋናቸውን በማቅረብ የተገኙ ግብዓቶች እጅግ ተፈላጊና የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ለሚደረገው ጥረት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ተናግረዋል፡፡

የእስራዔል ፖሊስ ኮሚሽን ድንበር ተሻጋሪ ወንጀሎችን በመከላከል፣በፖሊስ ሳይንስ ትምህርትና ስልጠና ኢንዲሁም በባለሙያና በልምድ ልውውጥ ዙሪያ ከኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር ለመስራት ፍላጎት ማሳየቱንም ምክትል ኮሚሽነር ጄነራሉ ገልጸዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ነሀሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *