አማዞን በህንድ የኦን ላይን የመድሃኒት ሽያጭን ጀመረ፡፡

የአለማችን ግዙፋ የኦላይን ግብይት መተግበሪያ አማዞን፣በህንድ የኦን ላይንም መድሃኒት ሽያጭን በባንጋሉሩ ከተማ መጀመሩንና በሂደት ወደ ሌሎች ከተሞችም እንደሚያስፋፋ ገልጧል፡፡

ኩባንያዉ ከኮሮና ቫይረስ ጋር ተያይዞ ሰዎች መድሃኒትን የመግዛትና መጠቀም ፍላጎት መጨመርን ከግምት ዉስጥ በማስገባት ስራዉን መቀላቀሉን ነዉ ያስታወቀዉ፡፡

ይህም ሰዎች በቤታቸዉ ሆነዉ የሚያስፈልጋቸዉን መድሃኒት እንዲሸምቱ እንደሚያስችላቸዉ የገለጸዉ ኩባንያዉ፣በባለሙያ ትዕዛዝ ብቻ የሚወሰዱ መድሃኒቶችን ለመግዛት ግን የግድ ባለሙያወ ትዕዛዝ የሰተበትን ኮድ ምስገባት ይኖርባቸዋል ነዉ ያለዉ፡፡

አማዞን መድሃኒትን በኦንላይን መሸጥ የጀመረዉ በአሜሪካ እ.ኤ.አ በ2017 ፒል ፓክ በሚል ሲሆን አሁን ላይ በእንግሊዝ፣ካናዳ፣አዉስትራሊያና በሌሎችን ሀገራት አገልግሎቱን እየሰጠ ይገኛል ሲል ቢቢሲ ዘግቧል።

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 8 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.