በአዲስ አበባ በቀጣዮቹ 3 ቀናት በከተማዋ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ መብራት እንደሚጠፋ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ለኢትዮ ኤፍ ኤም በላከው መግለጫ ከነገ ጀምሮ ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት እስከ ረፋዱ አራት ሰዓት ድረስ በከፍተኛ የኤሌክትሪክ ተሸካሚ መስመር ላይ የማሻሻያ ሥራ ለማከናወን ሲባል የኃይል አቅርቦት ይቋረጣል::

በነገው እለት የሀይል አቅርቦቱ ከሚቋረጥባቸው አካቢዎች መካከል፡፡

በአዲሱ ገበያ፣ በሰሜን ማዘጋጃ፣ በላዛሪስት ትምህርት ቤት፣ በሩፋኤል ቤተ-ክርስትያን፣ በገርጂ ኮንደሚኒየም በኢምፔሪያል ሆቴል፣ በገርጂ ጤና ጣቢያ፣ በዳችያ ቀለም፣ በገርጂ አንበሳ ጋራዥ እና አካባቢዎቻቸው፤ አንዲሁም ቦሌ መድሃኒዓለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ፣ በጎላጎል፣ በቺቺኒያ፣ በቦሌ ሚሊኒየም፣ በሳሚት ኮንደሚኒየም እስከ በፍየል ቤት፣በጊዮርጊስ ቤተ-ክርስትያን እና አካባቢዎቻቸው፤ረቡዕ ነሐሴ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ቀኑ 6፡00 ድረስ፡-

በዘነበወርቅ ቶታል፣ በአለርት ሆፒታል፣ በገርጂ ዩኒቲ ኮሌጅ፣ በቦሌ ሆምስ፣ በቦሌ ሲቪል አቬሽን፣ በጎሮ አለማየሁ ህንፃ፣ በጃክሮስ፣ በተወካዮች ምክር ቤት እና አካባቢዎቻቸው፣ እንዲሁም በራስ ደስታ ሆስፒታል፣ በእየሩሳላም ሆቴል፣ በእምቢልታ ሆቴል፣ በእንቁላል ፋብሪካ እና አካባቢዎቻቸው፣

በተጨማሪም ሀሙስ ነሐሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ከጠዋቱ 2፡00 እስከ ረፋዱ 4፡00 ድረስ፡-

በኢትዮ-ፕላስቲክ፣ በየነገው ሰው ትምህርት ቤት፣ በ17/24 ታክሲ ማዞርያ፣ በአዲሱ የወጣቶች ማዕከል ስታዲየም እና አካባቢዎቻቸው፣ እንዲሁም ከጠዋቱ 1፡00 እስከ ቀኑ 10፡00 ድረስ በቦሌ መድሀኒያለም ቤተ-ክርስትያን፣ በአያት ሆስፒታል፣ በብራስ ሆስፒታል፣ በሚሊኒየም አዳራሽ፣ በቦሌ ሚኒ እና አካባቢዎቻቸው፣
በመሆኑም ከወዲሁ አስፈላጊውን ጥንቃቄ አድርጉ ተብላችኋል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ሰኔ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *