ቡሩንዲ የቀድሞ ቅኝ ገዢዎቿ ጀርመን እና ቤልጂየምን 36 ቢሊዮን ዩሮ ካሳ ልትጠይቅ መሆኑን አስታወቀች፡፡

የምስራቅ አፍሪካዊቷ ሀገር ቡሩንዲ የቀድሞ የጀርመን ቅኝ ግዛት እንዲሁም ከ 60 ዓመታት በፊት ነፃነትን እስክትቀናጅ ድረስ በቤልጅየም የግዛት ዘመን ኖራለች፡፡

ዛሬ ይፋ የሆነ አንድ ሪፖርት እንዳመለከተው የሀገሪቱ መሪዎች ሁለቱ የቀድሞ ቅኝ ገዢ ሀገራት ላደረሱት ሁለንተናዊ ጥፋት 36 ቢሊዮን ዩሮ ካሳ እንዲከፍሉ ለመጠየቅ ማቀዳቸውን አትቷል፡፡

በርካታ ሚዲያዎችም ይህንኑ ሪፖርት ጠቅሰው ቤልጂየምና ጀርመን የቅኝ ግዛት ካሳ የሚሆን 42.6 ቢሊየን ዶላር እንዲከፍሉ ቡርንዲ የመጠየቅ እቅድ እንዳላት ነው ያነሱት።

የሀገሪቱ ሴኔት በቅኝ ግዛት ወቅት የተፈፀሙ ጉዳቶችን የሚገመግም አንድ ቡድን ማቋቋሙም ታውቋል ሲል ራዲዮ ፍራንስ ኢንተርናሽናል አውርቷል፡፡

መገናኛ ብዙሀኑ በሰራው ዘገባ ቡድኑ የጉዳቱ መጠን በግምገማው ከለየ በኋላ ቡሩንዲ እነዚህን ሰነዶች ለቤልጄምና ለጀርመን መንግስታት ለመላክ አቅዳለች ብሏል፡፡

ከዚህ በተጨማሪ ቡድኑ በወቅቱ የደረሱ ጥፋቶችን ከገመገመ በኋላ ለነዚህ የአውሮፓ ሀገራት ሰነዱን የመላክ እቅድ እንዳላት ተገልጿል፡፡

እንደ አውሮፓውያኑ ከ1890 ጀምሮ ጀርመን ቡሩንዲን በቅኝ ግዛትነት የያዘች ሲሆን ከሁለተኛው የአለም ጦርነት በኋላ ሀገሪቱ ነፃነቷን እስካገኘችበት 1962 ድረስ በቤልጄም ቅኝ ግዛት ስር ነበረች፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በደረሰ አማረ
ነሀሴ 11 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *