በአፍሪካ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት አንድም ሰው ያልሞተባቸው ኤርትራና ሲሸልስ ብቻ ናቸው፡፡

እስካሁን ድረስ በሁሉም የአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ሞት የተመዘገበ ሲሆን በኤርትራ እና በሲሸልስ ግን አንድም ሞት አልተመዘገበም፡፡

በኤርትራ እስካሁን 285 ሰዎች በይቫረሱ የተያዙ ሲሆን 248 ከቫይረሱ ሙሉ በሙሉ አገግመዋል፡፡

እንዲሁም 37 ሰዎች ደግሞ በለይቶ ማከምያ ክፍል ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ፡፡

በሀገሪቱ አንድም ሰው በጽኑ የታመመ እንደሌለ ነው የተገለጸው፡፡

እንዲሁም በሲሸልስ 127 ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ሙሉ በሙሉ በሚባል መልኩ 126 ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል፡፡

አንድ ሰው ብቻ ነው በለይቶ ማከምያ ክፍል ህክምናውን እየተከታተለ የሚገኝው፡፡

ከአፍሪካ አነስተኛ ሞት የተመዘገበባት ሀገር መካከለኛው ሰሀራ ስትሆን በሀገሪቱ አንድ ሰው ብቻ ነው ለህልፈት የተዳረገው፡፡

እንዲሁም በዚህችው ሀገር አስር ሰዎች ብቻ ናቸው በቫይረሱ የተያዙት፡፡

በጠቅላላው ቫይረሱ በሀገራቸው እንዳለ ሪፖርት ካደረጉ 215 የአለም ሀገራት በቫይረሱ ምክንት ሞት ያልተመዘገበባቸው ሀገራት 22 ብቻ ናቸው ሲል አልጀዚራ ዘግቧል፡፡

በሔኖክ ወ/ገብርኤል
ነሀሴ 12 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *