የኦሮሚያ ክልል የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ያወጣውን ሪፖርት ተቀባይነት እንደሌለው አስታወቀ።

የክልሉ መንግስት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው ሪፖርት ስህተትና መሬት ላይ ያለውን ነገር ያላገናዘበ ነው ብሏል።

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን በዛሬው እለት በኦሮሚያ ክልል የፀጥታ ሀይሎች ተመጣጣኝ ያልሆነ ሀይል ከመጠቀም ይቆጠቡ ሲል ማሳሰቡ የሚታወስ ነው፡፡

በክልሉ ለተቃውሞ በተጠሩ ሰልፎች ምክንያት የሚከሰተው የሰዎች ህይወት መጥፋት በእጅጉ እንደሚያሳስበውም ይናገራል ኮሚሽኑ፡፡

የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ምክትል ሀላፊ አቶ ግዛቸው ጋቢሳ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የኮሚሽኑ መግለጫ በጣም ስህተት እና ከእውነት የራቀ ነው፡፡

መሬት ላይ ያለው የዜጎችን ሰብአዊ መብት ለመጠበቅ የሚደረግ ጥረት ነው፡፡ግን የሚሰጠው መግለጫ ለሌላ አካል የሚያጎነብስ ነው ፡፡ሲሉም ያክላሉ አቶ ግዛቸው፡፡

ይህ ደግሞ በጣም የተሳሳተ እና ከኮሚሽኑ የማይጠበቅም ነው ብለዋል፡፡

የተጠራው አመጽ እና ያለፈውን አይነት ነውረኛ ተግባር እንዲፈጸም የሚሻ ነበር እንጂ ፈጽሞ ሰላማዊ ሰልፍ አይደለም ነው ያሉት አቶ ግዛቸው፡፡

እኛ በዚህ መግለጫ ደንግጠናል አዝነናልም ሲሉ አቶ ግዛቸው ተናግረዋል፡፡

መግለጫውን ያወጣው አካል ስፍራው ሳይሄድ ከማህበራዊ ድህረ ገጾች በተቃረሙ መረጃዎች በመሆኑ ትልቅ ስህተት ፈጽሟል ሲሉም ገልጸዋል፡፡

ተቋሙ ተከተለው መንገድ ስህተት ነው ፣ መግለጫው ለዜጎች ደህንነትም ስጋት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡

በመሆኑም ኮሚሽኑ ይህንን ሀላፊነት የጎደለው ስራ በቶሉ እንዲያርም ጠይቀዋል ፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 14 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.