ስዊድን በ150 ዓመታት በኋላ ከፍተኛ የተባለ ሞት መመዝገቡን ገለጸች፡፡

የሃገሪቱ ስታስቲክስ ቢሮ እንዳለዉ በ2020 ከጥር እስከ ሰኔ ባሉት ወራት ብቻ 51 ሽህ 405 ሰዎች ሲሞቱ ከ2019 በ15 በመቶ ወይም በ6 ሽህ 500 ከፍ ማለቱን ገልጿል፡፡

ይህ በሃገሪቱ እ.ኤ.አ በ1869 ከተከሰተዉና እርሱን ተከትሎ የ 55 ሽህ 431 ሰዎችን ህይወት ከቀጠፈዉ አደጋ ወዲህ እጅግ ከፍተኛዉ ነዉ ተብሏል፡፡

የሃገሪቱ የህዝብ ቁጥር እድገት ምጣኔ እየቀነሰ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን ወደ ሃገሪቱ የሚገቡ ስደተኞችም በዚህ ዓመት ቀደም ሲል ከነበረዉ በ 34 ነጥብ 7 በመቶ ቀንሷል፡፡

ስዊድን የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል በርካታ የአዉሮፓ ሀገራት የእንቅስቃሴ ገደቦችን ሲጥሉ፤እርሷ ይህን አላደረገችም፡፡

ትምህርት ቤቶች፣ካፌና ሬስቶራንቶች፣እንዲሁም የዉበት ሳሎኖች ስራቸዉን ሲያቀላጥፋ ነዉ አመቱን ያሳለፋት፡፡

በሃገሪቱ በኮሮና ቫይረስ ሳቢያ የሞቱ ሰዎች ቁጥር 5 ሽህ 802 ሲሆን ሌሎች ግን በምን ምክንያት ለሞት እንደተዳረጉ የአብዛኞቹ ሰዎች አይታወቅም መባሉን ሲ ኤን ኤን ዘግቧል፡፡

መላምቶች ግን ሀገሪቱ በኮሮና የተጠቁ ሰዎች ራሳቸዉን በቤታቸዉ ዉስጥ አግልለዉ ከቫይረሱ ለማገገም በሚያደርጉት ጥረት በርካቶች ህይወታቸዉን ሳያጡ እንዳልቀሩ ተናግረዋል፡፡

ሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *