በአሜሪካ እስከ መጪው ታህሳስ ድረስ 200 ሺህ ዜጎች በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ እንደሚችሉ የአገሪቱ የበሽታ መቆጣጠሪያ እና መከላከል ማዕከል አስታወቀ።

ሲኤንኤን በሰበር ዜናው እንደዘገበው በአሜሪካ እስከ መጪው ጥቅምት ድረስ 200 ሺህ አሜሪካዊያን በኮሮና ቫይረስ ሊሞቱ እንደሚችሉ ማዕከሉ ትንበያውን ይፋ አድርጓል።

ማዕከሉ ቫይረሱ በአሜሪካ በተከሰተባቸው ወራት ውስጥ 2 ነጥብ 4 ሚሊዮን አሜሪካዊያን በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን ሊያጡ ይችላሉ፣ በአጠቃላይም 60 ሚሊዮን አሜሪካዊያን በቫይረሱ ሊያዙ እንደሚችሉም ተንብዮ ነበር።

የማዕከሉ ዳይሬክተር ዶክተር ሮበርት ሬድፊልድ እስከ ዓመቱ መጨረሻ ታህሳስ ወር ድረስ የቫይረሱ ስርጭት ምን ሊመስል እንደሚችል ለአሜሪካ የህክምና ማህበር ተናግረዋል፡፡

እስካሁን ድረስ በአሜሪካ ውስጥ ከ 174 ሺህ በላይ ሰዎች እንደሞቱ እና ከ 5 ነጥብ 5 ሚሊዮን በላይ ሰዎች በበሽታው እንደተያዙ የጆንስ ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ አስታወቋል፡፡

በአሜሪካ ቫይረሱ አሁን ባለበት የስርጭት መጠን እና የመግደል መጠን በዚሁ ከቀጠለ በአመቱ መጨረሻ 200 ሺህ ያህል ሰዎች እንደሚሞቱ ግምቱን አስቀምጧል፡፡

ይህ የህይወት መጥፋት ትልቅ ኪሳራ ነው የሚሉት ሀላፊው ሁሉም ራሱን ሊጠብቅ ሊጠነቀቅ ይገባል ሲሉ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *