በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1ሺህ 200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ እየተሰራ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ።

ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት ወክለው የሚሰሩ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባቸውን የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ሚኒስቴሩ አስታውቋል

የሚኒስቴሩ ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ቃል አቀባዩ በዚህ ጊዜ እንዳሉት በየመን በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ያሉ 1ሺህ 200 ኢትዮጵያዊያንን ወደ አገራቸው ለመመለስ ከዓለም አቀፉ የፍልሰተኞች ድርጅት
IOM ጋር እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።

እነዚህ ዜጎች በየመን ያለው የእርስበርስ ጦርነት በተጨማሪ የኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ከባድ እንዳደረገባቸው አምባሳደር ዲና ተናግረዋል።

በመሆኑን እነዚህን ዜጎች ወደ አገራቸው ለመመለስ መረጃዎች እየተደራጁ መሆኑን ተናግረዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም ባለፉት ሁለት ሳንምታት ውስጥ ኢትዮጵያ የሁለትዮሽ እና ባለብዙ ወገን ውይይት መካሄዱን ተናግረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ገዱ አንዳርጋቸው ከአባይ ተፈሰስ ሀገራት ሚሲዮኖች ጋር የኢትዮጵያን ጥቅም የሚያስከበር ውይይት መካሄዱንም ገልጸዋል።

ቃል አቀባዩ አክለውም ኢትዮጵያን በተለያዩ አገራት ወክለው የሚሰሩ አምባሳደሮች ዓመታዊ ስብሰባቸውን የፊታችን ሰኞ ጀምሮ በአዲስ አበባ እንደሚሰበሰቡ ተናግረዋል።

በዳንኤል መላኩ
ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *