ትራምፕ አሜሪካን ጨለማ ዉሰጥ እንደከተቷት ጆ ባይደን ተናገሩ።

ለፕሬዝዳንታዊ ዉድድሩ ዲሞክራቶችን ወክለዉ የቀረቡት ጆ ባይደን በምርጫ ቅስቀሳቸዉ የትራምፕ ክፍተት ናቸዉ ያሏቸዉን ሁሉ በመጥቀስ እየተቹ ይገኛሉ፡፡

በዚህም ከምርጫ ቀደም ብሎ በተሰበሰበ ድምጽ ባይደን የተሻለ የማሸነፍ እድል እንዳላቸዉ ቢገመትም እስከ ምርጫዉ ድረስ ግን ትራምፕ ልዩነቱን አጥበብዉ በትረ ስልጣናቸዉን ይዘዉ ሊቀጥሉ እንደሚችሉም እየተነገረ ይገኛል፡፡

ባይደን በዊሊንግተን እና ዴላዌር ከተሞች ባደረጉት ንግግር እኔን ብትመርጡ እንደ ትራምፕ ወደ ጨለማ ሳይሆን ወደ ብርሃን እወስዳችኋለሁ፤ወደ ዉድቀት ሳይሆን እድገትን አረጋግጥላችኋለሁ ብለዋል፡፡

የምትመርጡትን ለዩ፤ተስፋ ወይስ ስጋት፣እዉነታ ወይስ ልብ ወለድ፣ እኩልነት ወይስ አድሏዊ አሰራር ይህን ከወዲሁ ወስኑ፤ምርጫችሁ ባይደን ከሆነ ተስፋ፣እዉነትና እኩልነትን እንደመረጣቸዉ ይሰማችሁ ሲሉም ነዉ በምርጫ ቅስቀሳቸዉ የተናገሩት፡፡

ባይደን ይህ ምርጫ አሜሪካ በቀጣይ ረዘም ላለ ጊዜያት ምን መምሰል እንዳለባት የሚወስን መሆኑን ገልጸዉ፤ሀገሪቱን ከገባችበት ጨለማ ዉስጥ ለማዉጣት በጋራ መቆም ያስፈልጋል ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ትራምፕ በበኩላቸዉ ቀደም ሲል ባይደንን አስመልክተዉ ባደረጉት ንግግር፣ባይደን የሚችሉት ንግግር ማሳመር ብቻ ነዉ፤ትክክለኛ ለዉጥ ያለዉ ከእኔ ጋር ብቻ ነዉ ማለታቸዉ ይታወሳል፡፡

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 15 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *