ቻይና ለኮቪድ-19 ተጋላጭ ለሆኑ ሰራተኞቿ የኮሮና ቫይረስ ክትባት መስጠት ጀመረች።

ቻይና ውጤታማ ነው የተባለውን ክትባት የኮሮና ቫይረስ ህሙማንን በማከም ላይ ለሚገኙ እና ለቫይረሱ በእጅጉ ተጋላጭ ለሆኑ ባለሙያዎች በመስጠት ላይ ትገኛለች ብሏል ሲኤን ኤን፡፡

የሀገሪቷ የጤና ኮሚሽን ከፍተኛ ባለስልጣን በሳምንቱ መጨረሻ ላይ እንዳስታወቁት ቻይና ከሐምሌ ወር ጀምሮ በከፍተኛ ደረጃ ተጋላጭ በሆኑ የስራ መስኮች ላይ ለሚሰሩ ባለሙያዎች የኮሮና ቫይረስ የሙከራ ክትባት ስትጠቀም ቆይታለች፡፡

የብሔራዊ ጤና ኮሚሽን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ልማት ማዕከል ዳይሬክተር የሆኑት ዚንግ ዙንግዌይ ቅዳሜ ዕለት ከቻይና የመንግሥት የዜና ተቋም ጋር ባደረጉት ቃለ-ምልልስም የሙከራ ክትባቱ ጥቅም ላይ እንዲውል መጽደቁን ተናግረዋል፡፡

ዜንግ ለ CCTV-2 እንዳሉት ለቫይረሱ የመጋለጥ እድላቸው ከፍተኛ ለሆኑት ባለሞያዎች ፤ የፊት መስመርን የሕክምና ባልደረቦቻችን ፣ የበሽታ መከላከያ ሰራተኞች ፣ የትኩሳት ክሊኒኮች ውስጥ ለሚሰሩ የህክምና ሰዎች እና የጉምሩክ እና የድንበር ሰራተኞችን ጨምሮ ክትባቱን እንዲወስዱ መወሰኑን አመልክተዋል፡፡

ክትባቱ የተመረተው በቻይና ብሔራዊ ባዮቴክ ግሩፕ ኩባንያ (CNBG.) ነው።

የዚህ ክትባት የደረጃ 3 ክሊኒካዊ ሙከራዎች በተባበሩት አረብ ኢመርትስ ፣ በፔሩ ፣ በሞሮኮ እና አርጀንቲና ተካሂደዋል፡፡

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 18 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *