በኡጋንዳ 150 የህግ ታራሚዎች በኮሮና ቫይረስ ተያዙ፡፡

የኡጋንዳ ባለስልጣናት እንዳሉት በሰሜናዊ የሀገሪቱ ክፍል በሚገኝ የገጠር ማረሚያ ቤት ውስጥ ከ150 በላይ የህግ ታራሚዎች እና አንድ ጥበቃ ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል፡፡

በተደረገ በቅርብ ጊዜ የታሰሩ ታራሚዎች የደቡብ ሱዳን ድንበር አቅራቢያ ወደ ሆነው አሙሩ ማረሚያ ቤት ከመወሰዳቸው በፊት በለይቶ ማቆያ ውስጥ እንዲቆዩ የተደረገ ሲሆን በዘህ ወቅት በላብራቶሪ ምርመራ ታራሚዎቹ ላይ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ባለስልጣናቱ ተናግረዋል፡፡

የኡጋንዳ የማረሚያ ቤቶች አስተዳደር በሀገሪቱ የሚገኙ ከ 60 ሺ በላይ የህግ ታራሚዎች እና ጠባቂዎቻቸውን የኮሮና ቫይረስ ምርመራ እንዲደረግላቸው የሀገሪቱን መንግስት ጠይቋል ፡፡

ማረሚያ ቤቶች የተጨናነቁ መሆናቸው ፣ በቂ የመገልገያ ቁሳቁሶች አለመኖሩ ለቫይረሱ መስፋፋት ከፍተኛ አስተዋፆ ሊኖረው ይችላል ሲሉም ስጋታቸውን ገልፀዋል፡፡

በኡጋንዳ እስካሁን 2 ሺ 362 ሰዎች በከሮና ቫይረስ ሜዛቸው የተረጋገጠ ሲሆን የ22 ሰዎች ሞትምመመዝገቡን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በሔኖክ አስራት
ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *