አልጄሪያውያን በቀጣዩ ህዳር በአዲሱ ህገመንግስት ላይ ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ቀጠሮ ይዘዋል፡፡

በአውሮፓውያኑ ህዳር 1 አዲስ በሚወጣው የሀገሪቱ ህገመንግስት ላይ ህዝበ ውሳኔ እንደሚካሄድ የተናገሩት የአልጀሪያው ፕሬዝዳንት ህዝበ ውሳኔው ዴሞክራሲን ለማጋገጥ እና ለሀገሪቱ ፓርላማ ተጨማሪ ስልጣን ለመስጠት ያለመ ነው ብለዋል፡፡

ባለፈው ዓመት ወደ ስልጣን የመጡት የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ፖሊቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ለማምጣት እንደሚሰሩ በተደጋጋሚ ሲናገሩ እንደነበር ዘገባው ጠቅሷል፡፡

አዲሱ ህገ-መንግስት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፓርላማው የሰሜን አፍሪካዊቷን ሀገር አልጄሪያ 45 ሚሊዮን ህዝብ ለመምራት የሚያስችል ተጨማሪ ስልጣን እንደሚሰጣቸውም ፕሬዝዳንቱ ተናግረዋል፡፡

በአዲሱ ህገመንገስት ላይ ህዝበ ውሳኔ ከመካሄዱ በፊትም ረቂቁ ለፓርላማ ቀርቦ ክርክር እንደሚደረግበትና ህዝበ ወሳኔ እንዲካሄድበት ውሳኔ እንደሚሰጥ ሚድልኢስት ሞኒተር ዘግቧል፡፡

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *