ውዳሴ ዲያግኖስቲክ የምርመራ መእከል ለአንድ ሺህ ዜጎች የነጻ የህክምና ሊሰጥ ነው።

ማእከሉ “ጳጉሜን ለጤና” በተሰኘ መጠሪያ ዘንድሮ ለ11ኛ ጊዜ ከፍለው መመርመር ለማይችሉ ዜጎች የነጻ ህክምና ማዘጋጀቱን አስታውቋል።

የምርመራ ማእከሉ ጳጉሜ ለጤና በሚል መሪ ቃል ላለፉት አስርት አመታት ሲሰራ የነበረውን ስራ በማስቀጠል ለ44 ሺህ 500 ዜጎች ምርመራ ያደረገ ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ ለአንድ ሺህ አቅመ ደካሞች ነጻ ህክምና ሊሰጥ መሆኑን የውዳሴ ዳያግኖስቲክስ ስራ አሰኪያጅ አቶ ዳዊት ሀይሉ ተናግረዋል።

ከምርመራ ዘመቻው በተጨማሪ 11ቀናትን የሚሸፍን መርሃ ግብር በመንደፍ ከጷጉሜ በፊት ያሉትን ቀናቶች በመጠቀም የተለያዬ የበጎ አድራጎት ስራዎችን ለመስራት መዘጋጀቱን ጨምረው ተናግረዋል።

የህክምና አገልግሎቱን ማግኘት የሚፈልጉ ዜጎች ከስር ባለውስልክ ቁጥር ማግኘት ይቻላል ብሏል።

0940050505 ወይም 0940040404 ይደውሉ ተብሏል።

በሔኖክ ወልደገብርኤል
ነሀሴ 19 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.