ከድምጻዊ ሀጫሉ ግድያ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ሁከት 67 ምዕመናን እንደተገደሉባት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን አስታወቀች።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በተፈጠረው ሁከት ምክንያት ተጎድተዋል ወደ ተባሉ አካባቢዎች ተሰማርታ ምልከታ ካካሄደች በኋላ በአዲስ አበባ መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽ/ቤት መግለጫ በመስጠት ላይ ትገኛለች።

ቤተ ክርስቲያኗ በዚህ ጊዜ እንዳለችው ከድምጻዊ ሀጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር ተያይዞ በኦሮሚያ ፣ በሐረሪ እና በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር በተፈጠረ ሁከት 67 ምዕመናን ሲገደሉ ከ7 ሺህ በላይ ሰዎች ደግሞ ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለዋል።

በአጠቀላይም ሁከቱን መነሻ በማድረግ ከ5 ቢሊዮን ብር በላይ የሚገመት የምዕመናን ንብረት መውደሙም በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

በኦሮሚያ ክልል፣በድሬዳዋ ከተማ አስተዳድር እና በሌሎች አካባቢዎች ምዕመናን በአሰቃቂ ሁኔታ ተገድለዋል፣ እንደ ሰውም አስክሬናቸው በክብር አልተቀበረም ፣ ሴቶች በባለቤታቸው፣በወንድምና በአባታቸው ፊት መደፈራቸው በምልከታ መረጋገጡ በመግለጫው ላይ ተገልጿል።

ጥቃቱ ሆን ተብሎ የኦርቶዶክስ ዕምነት ተከታዮችን በመለየት የተፈጸመ እንደነበር ያስታወቀችው ቤተ ክርስቲያኗ መንግስት ሕግን እንዲያስከብርም ጠይቃለች።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ነሀሴ 20 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.