እግር ኳስ በመጫወት ላይ ሳሉ በደረሰ የመብረቅ አደጋ የ10 ህጻናት ሕይወት አለፈ፡፡

በዩጋንዳ ዝናቡን ተከትሎ በተፈጠረው የመብረቅ ብልጭታ ኳስ በመጫወት ላይ የነበሩ አስር ህጻናት ሕወታቸው እንዳለፈ ነው የተገለጸው፡፡

ከሰሞኑ በሀገሪቱ ከፍተኛ ዝናብ ከመጣሉ ጋር ተያይዞ መጠኑ ከፍተኛ የሆነ የመብረቅ አደጋ እየተከሰተ እንደሚገኝ ነው የተነገረው፡፡

ህጻናቶቹ እግር ኳስ እየተጫወቱ ሳለ ከፍተኛ ዝናብ በመጣሉ ምክንያት እየተጠለሉ በነበሩበት ቦታ ነው አደጋው የደረሰባቸው፡፡

ሂወታቸው ካለፈው ህጻናት መካከል ዘጠኙ እድሜያቸው ከ13 እስከ 15 እንደሆነ እና ወድያውኑ ሂወታቸው እንዳለፈ ነው የተገለጸው፡፡

አንደኛው ህጻን ደግሞ ወደ ሆስፒታል እየተወሰደ ባለበት ቅጽበት ነው ሂወቱ ያለፍው፡፡

በዚህ አደጋ ምክንያት ሶስት ተጨማሪ ህጻናትም ከፍተኛ ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል እንደተኙ ነው መረጃዎች የሚጠቁሙት፡፡

በዩጋንዳ እንደዚህ አይነት አደጋ ደርሶ የነበረው በ2011 የነበረ ሲሆን ይሔኛው ከባዱ አደጋ ነው ተብሏል፡፡

በወቅቱ በአንድ ትምህርት ቤት ላይ በደረሰ የመብረቅ አደጋ ምክንያትም 18 ተማሪዎች ሂወታቸው አልፎ የነበረ ሲሆን በአጠቃላይ በዛ አመት በሀገሪቱ በመብረቅ አደጋ ምክንያት 28 ያህል ሰዎችም ለህልፈት ተዳርገው ነበር ሲል ቢቢሲ ዘግበቅል፡፡

በደረሰ አማረ
ነሀሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *