የዩጋንዳው ፕሬዘዳንት ዮሪ ካጉታ ሙሴቪኒ ሕልም አይቻለሁ በሚል ብሔራዊ የጸሎት ቀን አወጁ፡፡

የዩጋንዳው ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሶቪኒ በነገው ዕለት ብሔራዊ የጸሎት ቀን እንዲሆን አውጀዋል፡፡

ፕሬዝዳንቱ ለዚህ ውሳኔ የደረሱት አንድ የሀገራቸው ዜጋ የኮሮና ቫይረስ ጸሎት ሳደርግ እንደለቀቀኝ በህልሜ አይቻለሁ ባለው መሰረት ነው ተብሏል፡፡

በህልሜ ፈጣሪ ብሔራዊ የጸሎት ቀን እንዳዝ ነግሮኛል ለዛም ነው ብሔራዊ የጸሎት ቀን ለማወጅ የወሰንኩት ብለዋል ፕሬዝዳንቱ፡፡

በጸሎታችን ምክንያትም ከኮሮና ቫይረስ ሙሉ በሙሉ እንገላገላለን ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

በመሆኑም በዚህ የጸሎት ቀን ሁሉም ዜጋ እቤቱ ሆኖ ጸሎት ማድረግ አለበት ማለታቸውን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

የዩጋንዳ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ጥብቅ ክልከላ ቢያደርግም ቫይረሱን መከላከል አልቻለም እስካሁን ድረስም በሀገሪቱ 2ሺህ 600 ያህል ዜጎች በቫይረሱ ሲያዙ 28 ዜጎች ደግሞ ሂወታቸው አልፋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ ወ/ገብርኤል

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.