ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስልጣናቸውን በፈቃዳቸው የለቀቁት በገጠማቸው የጤና ምክንያት ሳቢያ መሆኑን አስታውቀዋል።
የጃፓኑ ጠቅላይ ሚንስትር ሽንዞ አቤ በዛሬው እለት በድጋሜ ወደ አንድ የቶኪዮ ሆሰፒታል በአንቡላስ ተወስደው ሰባት ሰዓታትን የፈጀ ምርመራ አድርገው ነበር፡፡
አቤ ባደረጉት ለሁለተኛ ጊዜ የሕክምና ምርመራ የጤናቸው ሁኔታ በስልጣናቸው ስለማያቆያቸው መልቀቃቸውን ሲኤንኤን ዘግቧል።
በሀገሪቱ ታሪክ ረጅም ዓመት ያስቆጠሩት እኚህ አቤ በአጎታቸው ልጅ ከተሾሙ በኋላ በርካታ አመታትን ስልጣን ላይ ቀይተዋል፡፡
በያይኔ አበባ ሻምበል
ነሀሴ 22 ቀን 2012 ዓ.ም











