ስናይፐሩ የተያዘው በተበታተነ መልኩ በቦርሳዎች ከሌሎች እቃዎች ጋር ተጠቅልለው እንደነበር ተገልጿል።
በቀን 25/12/12 በቦሌ ኤርፖርት አለማቀፍ በረራ መግቢያ በኩል ከሳዑዲ አረብያ የመጣ አንድ ግለሰብ ከኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ቆንጽላ ጽ/ቤት ጅዳ ጠቅልለዉ ወደ ሀገራቸዉ እንደሚገቡና የሚይዙት የግል መገልገያ ዕቃ ከቀረጥና ታክስ ነፃ እንዲሆንላቸዉ ደብዳቤ መያዛቸው ተገልጿል።
ግለሰቡ ይህንኑ አጋጣሚ በመጠቀም ከግል መገልገያ ዕቃዎቻቸዉ ጋር ተገጣጥሞ ለ7 የስናይፐር ጦር መሳሪያ የሚሆኑ ክፍሎችን በታትኖ በተለያዩ ሻንጣዎች ዉስጥ ደብቀዉ ለማሳለፍ ሲሞክሩ በቦሌ ኤርፖርት ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት አማካኝነት በቁጥጥር ስር መዋሉን ኢትዮ ኤፍ ኤም ከድርጅቱ ሰራተኛ ሰምቷል።
ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም











