በአዲስ አበባ በአምሰት ክፍለ ከተሞች ብቻ ከ210 ሺህ ካሬ ሜተር በላይ መሬት መወረሩን ኢዜማ አስታወቀ።

ፓርቲው አደረኩት ባለው ጥናት በ2012 በጀት ዓመት መስከረም ወር ላይ ለባለዕድለኞች ወጥተዋል ያላቸው ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች መተላለፉንም አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ በአዲስ አበባ ህገወጥ የመሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች እደላን በሚመለከት ለአንድ ወር አደረኩት ያለውን የጥናት ግኝት ዛሬ ይፋ አድርጓል።

እንደ ፓርቲው ጥናት መሰረት ከሆነ በአዲስ አበባ አምስት ክፍለከተሞች ማለትም የካ፣ቦሌ፣ኮልፌ ቀራኒዮ፣ንፋስ ስልክ ላፍቶ እና አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተሞች ከ210 ሺህ በላይ ካሬ ሜትር ቦታዎች በመንግስት አመራሮች ድጋፍ ተወረዋል።

ይህ መሬት ገሚሱ በመንግስት ተቋማት ድጋፍ ጭምር ካርታ ወጥቶላቸው በህገወጥ መንገድ ስማቸው እንዲዘዋወር ሲደረግ ገሚሶቹ ደግሞ አሁንም ታጥረው ተቀምጠዋል።

የጋራ መኖሪያ ቤቶችን በሚመለከት መስከረም 2012 ዓም ለባለእድለኞች እጣ ወጥቶባቸው የነበሩ ከ95 ሺህ በላይ የጋራ መኖሪያ ቤቶች ቤቱ ለሚገባቸው ሰዎች አልተላለፉም ብሏል።

እነዚህ ቤቶች ከአዲስ አበባ ውጪ ወደ አዲስ አበባ ለመጡ ሰዎች፣ለአመራሮች እና ሌሎች ቤቱ ለማይገባቸው ሰዎች ተላልፈዋል ብሏል ፓርቲው።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *