በጋምቤላ ክልል በጆር ወረዳ በጎርፍ ምክንያት ከስድስት ሺህ በላይ ሰዎች ከቤት ንብረታቸው መፈናቀላቸው ተገለጸ፡፡

የክልሉ ፕረስ ሴክረታሪያት ጽ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳስታወቀው በጆር ወረዳ በተከሰተ ጎርፍ ከ6 ሺህ በላይ ሰዎች ተፈናቅለዋል።

የክልሉ ዕርሰ መስተዳደር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በቦታው ድረስ በመገኘት በጎርፉ ምክንያት የተጎዱትን ማህበረሰብ ምልከታ አድርገዋል፡፡

ችግሩን ለመቅረፍ ዘላቂነት ያለው ስራ እየተሰራ መሆኑንም ፕሬዘዳንቱ አስታውቀዋል፡፡

አያይዘውም በአሁን ወቅት ለተጎጂዎች እየተደረገላቸው ያለው ድጋፍ በቂ ያለመሆኑን ገልጸው የሚመለከታቸው አካላቶች ሁሉ ለረባረቡ እንደሚገባ አሳስበዋል።

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *