ኢትዮጵያ በቀጣዮቹ 10 ዓመታት ውስጥ በአምስት መስመሮች ከ3 ሺህ በላይ ኪሎ ሜትር የባቡር ሀዲድ ለመገንባት ማቀዷን አስታወቀች።

የትራንስፖርት ሚኒስቴር እንዳስታወቀው የባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታ አሁን ካለበት 902 ኪሎ ሜትር ወደ 4ሺ ኪሎ ሜትር ለማድረስ እቅድ ተነድፏል።

የትራንስፖርት ዘርፉን ለማዘመንና የተጓዦችን ደህንት ከመጠበቅ አንፃር ከፍተኛ አስተዋፆ ይኖረዋል የተባለለት የ10 ዓመት የትራንስፖርት ዘርፍ መሪ እቅድ ተዘጋጅቷል፡፡

ኢትዮ ኤፍ ኤምም በ10 ዓመት መሪ እቅዱ መሰረት የካርቦን ልቀትን የሚቀንሰው የኤሌክሪክ የባቡር መስመር ዝርጋታ የት ይደርሳል? ሲል ሚኒስቴሩን ጠይቋል፡፡

በሚኒስቴሩ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ እንዳልካቸው ፀጋዬ ለጣቢያችን ሲመልሱ አሁን ያሉትን በቀጣይ አስር ዓመት የባቡር መሰረተ ልማት ዝርጋታን ወደ 4ሺ ኪሎ ሜትር ለማድረስ እንዲሁም የሰዎች የማጓጓዝ አቅምንም ከ200 ሺህ በላይ ለማድረስ ታቅዷል ብለውናል፡፡

በቀጣይ 10 ዓመታት ውስጥ ይገነባሉ ከተባሉት የባቡር መሰረተ ልማቶች መካከል የመጀመሪያው ከወልዲያ ተነስቶ ወረታ፣መተማ እስከ ሱዳን ድንበር የሚገነባው አንዱ ነው።

ሁለተኛው የባቡር መስመር ግንባታ ደግሞ ከመቀሌ እስከ አሰብ ወደብ ድረስ የባቡር ሀዲድ የሚገነባ ሲሆን ሶስተኛው ከሞጆ፣ ሀዋሳ፣ወይጮ ፣ ሞያሌ ድረስ ነው ተብሏል፡፡

4ተኛው የባቡር መሰረተ ልማት ደግሞ ከሰበታ ተነስቶ ወደ ኢጃዲ፣ ጅማ፣በደሌ እስከ ደቡብ ሱዳን ድንበር ይደርሳል ተብሏል፡፡

5ተኛው የባቡር መሰረተ ልማት ፕሮጀክት ደግሞ ከአይሻ -በርበራ ወደብ ድረስ ይዘረጋል ተብሏል፡፡

በተጨማሪም አዲስ አበባ ላይ የቀላል ባቡር ማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እንደሚኖሩ የተነገረ ሲሆን የአዋጪነት ጥናት ሲጠናቀቅ ለፕሮጀክቶቹ የተያዘው በጀት ይፋ ይሆናም ተብሏል፡፡

በተጨማሪም ከጅቡቲ ወደ ኢትዮጲያ ያለው የባቡር ጭነት የማመላለስ አቅምንም ከ1 ነጥብ 35 ሚሊየን ቶን ወደ 5 ሚሊየን ቶን ለማድረስ የታቀቀደ ሲሆን በቀን መስመር ላይ የሚሰራ የጭነት ባቡር መጠንንም ከ1 ነጥብ 5 ሚሊየን ቶን ወደ 6 ሚሊየን ቶን ማሳገድ በመሪ አቅዱ ተካቷል፡፡

በአዲስ አበባ ቀላለ ባቡር ያለውን በቀን 120 ሺ ሰው የማጓጓዝ አቅምንም ወደ 200 ሺ ለማድረስ መታቀዱ ተገልጿል።

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.