የመጀመርያው ታሪካዊው የንግድ አይሮፕላን ከእስራኤል ተነስቶ የተባበሩት አረብ ኤምሬት አርፏል።

ኤል አል አየር መንገድ የአሜሪካንና የእስራኤልን ተወካዮች ይዞ የሶስት ሰአት በረራ በማድረግ የተባበሩት አረብ ኤምሬት መድረሱን ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

በረራው ለእስራኤል የተከለከለ የነበረውን የሳኡዲ አረቢያ የአየር ክልል እንዲያልፍ ተፈቅዶለታል፡፡

ከተመሰረተችበት እንደ አውሮፓውያኑ 1948 ጀምሮ ፤ ከመካከለኛው ምስራቅ ሀገራት እስራኤልን እንደ ሀገር እውቅና የሰጠቻት የመጀመርያዋ ሀገር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ነች፡፡

ቅዳሜ ነበር የተባበሩት አረብ ኤምሬት ከ 1972 ጀምሮ በስራ ላይ የነበረውን ከእስራኤል ጋር የንግድም ማህበራዊም ሆነ ማንኛውንም ግንኙነት እንዳይደረግ የሚደነግገውን ህግ ያነሳችው፡፡

በዚህ ወር መጀመርያም ነበር ሁለቱ ሀገራት ቀጥታ የስልክ ግንኙነት ለመጀመርያ ጊዜ የጀመሩት፡፡

በአሜሪካ አደራዳሪነት ግንኙነታቸውን ጤናማ ለማድረግ የደረሱትን ስምምነት ለህዝብ በድንገት በማሳወቅ ያስደመሙት እደ አውሮፓውያኑ ነሐሴ 13 ነበር፡፡

በረራው የዶናልድ ትራምፕ የልጅ ባልና ከፍተኛ አማካሪያቸውን ጃሬድ ኩሽነር እንዲሁም የእስራኤል የብሔራዊ ደህንነት አማካሪ ሜር ቤን ሻባት ጨምሮ የተለያዩ ወኪሎችን ይዞ ነበር፡፡

ለእስራኤልና ለተባበሩት አረብ ኤምሬት ስምምነት የትራምፕ ከፍተኛ አማካሪ ጃሬድ ኩሽነር ሚስጥራዊ ውይይት ሲያደርጉ ከርመዋል፡፡

ይሄ ከሁለቱ ሀገራት የተወከለ ጥንድ ቡድን የተባበሩት አረብ ኤምሬት ተወካዮችን የሚያገኝ ሲሆን ሀገራቱ ተባብረው ሊሰሩ የሚችሉባቸው መስኮች ላይ ይወያያሉ ተብሏል፡፡

በሔኖክ አስራት
ነሀሴ 25 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *