በቶጎ የመጀመርያዋ ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ተመረጠች፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የቶጎው ፕሬዝዳንት በሀገራቸው ታሪክ የመጀመርያዋን ሴት ጠቅላይ ሚኒስትር ሹመትን ሰጡ፡፡ የ60 አመቷ ቪክቶሪ ቶሜጋ ዶግቤ የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው በፕሬዝዳንቱ አማካኝነት ሹመት አግኝተዋል፡፡ ዶግቤ የቀድሞ የሀገሪቱን ጠቅላይ ሚኒስትር የነበሩትን ኮሚ ሴሎምን ተክተው ነው ጠቅላይ ሚኒስትር የሆኑት፡፡ ኮሚ ሴሎም ባለፈው አርብ እለት በገዛ ፍቃዳቸው ከስልጣናቸው መነሳታቸው ይታወሳል፡፡ ኮሚ ሴሎም ከ2015 አንስቶ እስካሁን የቶጎ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው […]

አዘርባጃን እና አርሜኒያ ወደ ግጭት ከገቡበት ቀን አንስቶ እስካሁን 2 ሺህ 300 የአርሜኒያ ወታደሮች መሞታቸው ተነገረ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

የአርሜኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር እንደተናገሩት ግጭቱ ከተቀሰቀሰበት አንስቶእስካሁን ድረስ 2ሺህ 300 ያህል ወታደሮች ሂወታቸው እንዳለፈ ነው የተናገሩት፡፡ አናዱሉ የዜና ወኪልም ሁለቱ ሀገራት ወደ ለየለት ጦርነት መግባታቸውን ጠቅሶ በርካታ ንጹሀን ዜጎች የግጭቱ ሰለባ እየሆኑ ይገኛሉ ሲል አስታውቋል፡፡ ከአራት ቀናት በፊት ነበር ሁለቱ ሀገራት በታሪክ እየተወዛገቡበት ባለው የናጎሮኖ ተራራ የይገባኛል ጥያቄ ምክንያት ግጭት ውስጥ የገቡት፡፡ በዚህችው ተራራ […]

ጀርመን ለኢትዮጵያ 4 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር እርዳታ ሰጠች።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ጀርመን እርዳታውን የሰጠችው ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ስራዎችን ለመደገፍ ነው። የእርዳታ ስምምነቱ ዛሬ በገንዘብ ሚንስቴር አዳራሽ በአቶ አህመድ ሽዴ እና በኢትዮጵያ የጀርመን አምባሳደር ስቴፈን አወር ተፈራርመዋል። ጀርመን የኢትዮጵያን የልማት ስራዎች ከሚደግፉ የአውሮፓ ህብረት አባል አገራት መካከል ዋነኛዋ አገር ናት። ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8 በሳሙኤል […]

ለአገር ክብር ዋጋ የሚከፍል ዘመናዊ የፖሊስ ሰራዊት መገንባቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተናገሩ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የፌደራል ፖሊስ ኮምሽን ከራስ በላይ ለህዝብና ለሃገር በሚል መሪ ቃል በዛሬው እለት በመስቀል አደባባይ የተለያዩ ትርኢቶችን አቅርቧል፡፡ በትርኢቱም የተለያዩ የፀረ ሽብር ተግባራት ሲከሰቱ ፈጣን ምላሽ በመስጠትና ውስብስብና የተቀነባሩ ወንጀሎችን ለማክሸፍ የሚረዱ እንደሂሁም የፌደራል ሰራዊት አባላቱ አሁን ያሉበትን ደረጃ የሚያሳዩ የተለያዩ ወታደራዊ ትእይቶችን አሳይተዋል፡፡ በተለይም የኮማንዶ አባላቱ ለሃገር ደህንነትና ሰላም ከፊት በመሰለፍ የትኛውንም ህገ ወጥ ጥቃትን […]

ትራምፕና ባይደን የ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ክርክር አካሄዱ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕና እጩ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ለ2020 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ የመጀመሪያውን የገፅ ለገፅ ክርክራቸው ማካሄድ ጀምረዋል፡፡ በርካቶች በተከታተሉት በዚሁ ክርክር በትራምፕና ባይደን በርካታ የሓሳብ ፍጭቶች ተነስተዋል፡፡ በተለይም በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ክፍኛ እየተጎዳች ላለችው አሜሪካ ተገቢውን ምላሽና ሃላፊነት አልሰጡም ተብለው በተቃዋሚያቸው ጆን ባይደን ለትራምፕ ለተነሳውን ሃሳብ፤ትራምፕ የባይደንን ሃሳብ ውድቅ ከማድረግ አልፈው ባይደንን ምንም እንኳን በጣም ታሳዝናክ […]

ከአፍሪካ በስውር ወደ ሌሎች የዓለማችን አገራት የሚወጣው አመታዊ ገንዘብ ከ50 ቢሊዮን ወደ 89 ቢሊየን ዶላር ከፍ ማለቱን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አስታወቀ፡፡

Posted Leave a commentPosted in የውጭ ዜና

አህጉሪቷ በዋናነት ገንዘቡን የምታጣው በሙስና በታክስ ማጭበርበር እና በስርቆት እንደሆነ ነው የድርጅቱ ሪፖርት ያመላከተው፡፡ አፍሪካ ይህንን መጠን ያለው ገንዘብ የምታጣው ከሌሎች ሀገራት ጋር በምታደርገው የንግድ ልውውጥ ነው፡፡ ድርጅቱ ከአምስት አመታት በፊት በአዲስ አበባ በተደረገው ስብሰባ ላይ በተመሳሳይ መልኩ 50 ቢሊየን ዶላር በስወራ ታጣ እንደነበረ አስታውቆ ነበር፡፡ በመሆኑም በየአመቱ ከፍተኛ ገንዘብ በስወራ መልኩ እንደምታጣ ነው ሪፖርቱ […]

ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማሪያም አረፉ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

በኢትዮጵያ የፖለቲካ ታሪክ የተለያዩ ጥናቶችን በማካሄድ የሚታወቁት ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም በ91 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል። ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8 ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያውያንመስከረም 20 ቀን 2013 ዓ.ም

እውን የፋና ላምሮት 8222 የአጭር የጽሁፍ መልዕክት መቀበያ ስራ አቁሞ ነበር?

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን በ11 ዙሮች ሲያካሂደው የነበረውን የፋና ላምሮት የሙዚቀኞች ውድድር ባሳለፍነው ሳምንት እሁድ መስከረም 17 ቀን 2013 ዓ.ም ማጠናቀቁ ይታወሳል። ግማሽ ሚሊዮን ብር በሚያሸልመው በዚህ ውድድር የመጨረሻው ዕለት በተደረገ ውድድር መቅደስ ግርማ በአንደኝነት ኤልያስ ተክለሀይማኖት ሁለተኛ እንዲሁም ዮናታን ክብረት በሶስተኛነት ማጠናቀቃቸውም አይዘነጋም። ይሁንና በውድድሩ ፍጻሜ ላይ ተመልካቾች በአጭር የጽሁፍ መልዕክት የሚሰጡበት 8222 መበላሸቱ በመድረኩ […]

ትምህርት ሚኒስቴር ሁለት የግል ትምህርት ቤቶችን አገደ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ተከትሎ ትምህርት ሚኒስቴር ያወጣውን የክፍያ መመሪያ ተላልፈው የተገኙ ሁለት የግል ትምህርት ቤቶች ለግዜው መታገዳቸውን የትምህርት ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡ እገዳው የተላለፈባቸው ትምህርት ቤቶች አንድነት ኢንተርናሽናል እና ሄሌኒክ-ግሪክ ማህበረሰብ ት/ቤት ናቸው፡፡ በ ትምህርት ቤቶቹ ላይ ውሳኔ የተላለፈው ትምህርት ቤቶቹ የተቀመጠውን መመሪያ ተግባራዊ ባለማድረጋቸው የወላጅ ኮሚቴዎች ተደጋጋሚ አቤቱታ በማቅረባቸው መሆኑም ተገልጿል፡፡ ትምህርት ቤቱ ከዛሬ ጀምሮ መንግስት( […]

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን በሲሲቲቪ እና በድሮን የታገዘ የጸጥታ ጥበቃ ስራዎችን ሊያከናውን መሆኑን አስታወቀ።

Posted Leave a commentPosted in የሀገር ውስጥ ዜና

ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽ ለመስጠት የሚስያችሉ ቴክኖሎጂዎችን ሊጠቀም መሆኑን አስታውቋል፡፡ ኮሚሽኑ ለህዝብ ጥያቄ ፈጣን ምላሽና አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችሉ ዘመናዊ ቴክኖሎጂዎችን ማሟላት ቀጣይ የትኩረት አቅጣጫው መሆኑን አስታውቋል፡፡ የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር አቶ ጀይላን አብዲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የወንጀል መከላከል ስራን በሲሲ ቲቪ ካሜራ የተደገፈ እንዲሆን ማድረግ፣ዘመናዊ የመገናኛ ራዲዮችን መጠቀም እንዲሁም ለወንጀል ምርመራ የሚስያፈልጉ በተለይ […]