ኢዴፓ በፍርድ ቤት ነጻ የተባሉትን አቶ ልደቱ አያሌው ከእስር ባለመለቀቃቸው “አካልን ነጻ የማድረግ” ክስ ሊመሰርት መሆኑን አስታወቀ።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም አቶ ልደቱ አያሌው የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት በትናንትናው ዕለት መዝገቡን ዘግቶ ነጻ መሆናቸውን ቢያሳውቅም እስካሁን ከእስር አልተፈቱም።

ፖሊስ አቶ ልደቱን እንዲፈታ እና የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ለምን አይከበርም ብለን ስንጠይቅ ይሄ አሰራራችን ነው የሚል ምላሽ ተሰጥቶናል የሚሉት አቶ አዳነ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ፖሊስ የፍርድ ቤቶችን ትዕዛዝ አለማክበር እየተለመደ መጥቷል ብለዋል።

በዚህም መሰረት አቶ ልደቱ አያሌውን ከእስር ለማስፈታት ” አካልን ነጻ ማውጣት” የተሰኘ ክስ ለአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሊያስገቡ መሆኑንን ሊቀመንበሩ አስታውቀዋል።

ፓርቲው ክሱን ለመመስረት በዛሬው እለት ከህግ ባለሙያዎቻችን ጋር በመነጋገር ላይ ነን ሲሉም ተናግረዋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻምበል
ነሀሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *