የኮሮና ቫረስ ከአለማችንን ሀገራት የ90 በመቶውን የጤና ስርአት ማዛባቱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታወቀ።

የኮሮና ቫይረስ አብዛኛዎቹን የአለም ሀገራት የጤና ስርአት ማዛበቱን የአለም የጤና ድርጅት ገልጿል፡፡

መረጃው የተሰበሰበው በመጋቢት እና በሰኔ ወር መካከል ነው ብሏል ቢቢሲ በዘገባው ፡፡

በቫይረሱ ጫና ምክንያት ብዙ መደበኛ ቀጠሮዎች እና ምርመራዎች ተሰርዘዋል ፣ ወረርሽኙ የካንሰር ህክምናን ጨምሮ ከፍተኛ ክብካቤን የሚሹ ታማሚዎችን በእጅጉ ነክቷል ፡፡

የመካከለኛ እና ዝቅተኛ ገቢ ያላቸው ሀገሮች ከፍተኛ የሆኑ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎችን አስመዝግበዋል፡፡

ከግማሽ በላይ በሆኑ አገራት ውስጥ የእርግዝና መከላከያ እና የቤተሰብ ዕቅድ አገልግሉት 68 በመቶ ተጎድቷል ተብሏል።

በተጨማሪም የአእምሮ ጤና ችግሮች 61 በመቶ እንዲሆም የካንሰር ሕክምና 55 በመቶ መዛባቱን ነው የተናገረው ፡፡

የህይወት አድን የድንገተኛ ህክምና አገልግሎቱች በሩብ ያህል ሀገራት ተጽዕኖ እንዳሳረፈ ድርጅቱ አስታውቋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔ አበባ ሻምበል
ነሀሴ 26 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *