በአዲስ አበባ አንድ ሹመኛ 140 ሺህ ብር ጉቦ ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ ተያዙ።

ጉቦውን ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ የተያዙት በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ እና ቁጥጥር ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ናቸው።

ሃላፊው እጅ ከፍንጅ የተያዙት ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ መሆኑን የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽህግፈት ቤት ነው።

አቶ ኤፍሬም አለሙ የተባሉ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወረዳ 03 አስተዳደር የግንባታ ፍቃድ ጽኅፈት ቤት ሃላፊ ለተገልጋይ ህገ ወጥ የግንባታ ፍቃድ ለመስጠት 140 ሺህ ብር ሲቀበሉ እጅ ከፍንጅ በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ባለጉዳዩ ለከንቲባ ጽ/ቤት እና ለአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ባደረሰው ጥቆማ ከህብረተሰቡ ጋር በመተባበር በተደረገ ክትትል የጽህፈት ቤት ሃላፊውን ገንዘቡን ሲቀበል በቁጥጥር ስር መዋሉን በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ የወንጀል ክትትል ሃላፊ ኮማደር አወሉ አህመድ ተናግረዋል፡፡

ጥቆማውን ያደረሱንን ግለሰቦችን እያመሰገንን ህብረተሰቡ ህጋዊ ለሆነ አገልግሎት ጉቦ መሰል እጀ መንሻ የሚጠይቁ የመንግስት መዋቅር ላይ ያሉ አካላትን በማጋለጥ እና ጥቆማ በመስጠት ግዴታውን እንዲወጣ የከተማ አስተዳደሩ ጥሪውን አቅርቧል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ነሀሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.