ኢን ኤን አዉት ኢትዮጵያ በርገር መለያዉን ቀየረ።

ላለፋት 10 አመታት IN-N-OUT በሚል የበርገር ምርቶችን ለደንበኞቹ ሲያቀርብ የቆየዉ ድርጅቱ አሁን መለያዉን ወደ IN-JOY ቀይሯል፡፡

በ 200 ሽህ ብር ስራዉን የጀመረዉ IN-N-OUT በርገር አሁን የካፒታል መጠኑን 200 ሚሊዮን ብር ማድረሱን የድርጅቱ ባለቤት አቶ ሳለአምላክ አንዳርጌ ተናግረዋል፡፡

ድርጅቱ መለያዉን የቀየረዉም ዓለም ዓቀፍ የበርገር ገበያን ለመቀላቀል በሚንቀሳቀስበት ወቅት ይህን የንግድ ምልክት የሚጠቀም ሌላ ድርጅት በመኖሩ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

አሁን ኢን-ጆይ በሚል መለያዉ የአፍሪካ ብራንድ ለመሆን እንደሚሰራ የተናገሩት አቶ ሳለአምላክ፣ በቅርቡ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በሃገር ዉስጥ በባህር ዳር፣ሃዋሳ፣ጎንደርና መቀሌ ቅርንጫፎችን የመክፈት እቅድ ሲኖረዉ በዉጭ ደግሞ በኬንያ ናይሮቢና በዱባይ ቅርንጫፎቹን እንደሚከፍት አስታዉቀዋል፡፡

የቀድሞዉ ኢን-ኤን-አዉት የአሁኑ ኢን-ጆይ በርገር ሰባት ቅርንጫፎች ሲኖሩት 300 ለሚሆኑ ሰራተኞች ደግሞ የስራ እድል ፈጥሯል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *