የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቃቢ ህግና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አቀርባለሁ ያሉትን ማስረጃ ባለማቅረባቸው ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጠ።

የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀመንበር አቶ አዳነ ታደሰ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንዳሉት የቢሾፍቱ ከተማ ፍርድ ቤት ዛሬ ከቀኑ 8 ሰዓት ላይ በዋለው ችሎት አቃቤ ህግና ፖሊስ በ አቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ቢጠይቅም አቃቤ ህግ ና ፖሊስ ማስረጃውን አላቀረቡም፡፡

በመሆኑም ፍርድ ቤቱ አቃቤ ህግ ና ፖሊስ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ አለን ያሉትን ማስረጃ እንዲያቀርቡ ለነገ ጠዋት ተለዋጭ ቀጠሮ መስጠቱን አቶ አዳነ ነግረውናል።

ፍርድ ቤቱ በጠዋቱ ቀጠሮው ማስረጃውን አይቶ ከሰዓት 8 ላይ ውሳኔ እስጥበታለሁ ማለቱን አቶ አዳነ ለጣቢያችን ተናግረዋል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በያይኔአበባ ሻንበል
ነሀሴ 28 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *