መምህራን ትምህርትና ፖለቲካን ከማቀላቀል ድርጊት እንዲቆጠቡ የአሜሪካ ፖሊስ አስጠነቀቀ፡፡

በአሜሪካ የኦታህ ግዛት ፖሊስ ማህበር ባስተላለፈዉ ማስጠንቀቂያ አዘል መልክዕት፣መምህራን ወደ ትምህርት ቤት ሲገቡ የፖለቲካ አጀንዳቸዉን ወደ ጎን በመተዉ ማስተማሪያ መጻህፍትን ይዘዉ መግባት አለባቸዉ፤ለሁሉም ሜዳ አለዉ ብሏል፡፡

ፖሊስ ይህን ያለዉ የአንድ የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህር የጥቁሮች ህይወት ይመለከተኛል/ “Black Lives Matter”/ ጽሁፍ ያለበት ቲሸርት ለብሶ ወደ ትምህርት ቤት ገብቶ መገኘቱን ተከትሎ መሆኑን ስካይ ኒውስ ዘግቧል።

በዚህም መምህራን የፖለቲካ አመለካከታቸዉን በታዳጊ ህጻናት ላይ ከመጫን እንዲቆጠቡና የመማር ማስተማር ስራቸዉን ብቻ አከናዉነዉ ፖለቲካዉን በፖለቲካ ሜዳዎች ብቻ እንዲያከናዉኑ አሳስቧል፡፡

በግዛቲቱ ህግ መሰረት መምህራን ምንም አይነት የግላቸዉን የፖለቲካም ሆነ ሃይማኖታዊ አስተያየት ለተማሪዎቻቸዉ ማስተላለፍ አይችሉም፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሙሉቀን አሰፋ
ነሀሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published.