የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መከላከያ 77 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ አደረገ።

የአሜሪካ ተራድኦ ድርጅት ወይም ዩኤስ ኤይድ በኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል የሚውል 77 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ማድረጉን የጤና ጥበቃ ሚኒስትሯ ዶክተር ሊያ ገልጸዋል።

የድርጅቱ ሀላፊዎች ድጋፉን ዛሬ ረፋድ በአዲስ አበባ ለኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስረክበዋል።

ድርጅቱ ኢትዮጵያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል የምታደርገውን ጥረት እንደሚደግፍም በትዊተር ገጹ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ እስከ ትናንትናው ዕለት ድረስ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 55 ሺህ 213 ሲደረስ 856 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ምክንያት ህይወታቸውን እንዳጡ የህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት መረጃ ያስረዳል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ነሀሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *