ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በአስራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ ለጳጉሜ 2/2012 ዓ/ም እንዲያቀርብ ቀጠሮ ሰጠ።

ፖሊስ ለዛሬ ነሃሴ 29/2012 ዓ/ም በአሥራት ጋዜጠኞች ላይ አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ቀጠሮ ተሰጥቶት የነበር ቢሆንም ሳያቀርብ መቅረቱ ተገልጿል።

በዛሬው ችሎት ፖሊስ ተጨማሪ 14 ቀን እንዲሰጠው ጠይቆ የነበር ቢሆንም የተከሳሾቹ ጠበቃ ፖሊስ በተደጋጋሚ እያስቀጠረ መረጃ ማቅረብ አለመቻሉን ጠቅሰው ተቃውመዋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ ለጳጉሜ 2/2012 አለኝ የሚለውን መረጃ እንዲያቀርብ ተጨማሪ 3 ቀን ፈቅዷል።

በሌላ በኩል ባለፉት የችሎት ውሎዎች ፍርድ ቤቱ የአሥራት ጋዜጠኞች የእስር ቤት አያያዝ እንዲሻሻል ትዕዛዝ ሰጥቶ የነበር ቢሆንም ትዕዛዙ እንዳልተከበረ ጋዜጠኞቹ እና ጠበቃቸው ለፍርድ ቤቱ ተናግረዋል።

ፍርድ ቤቱም ፖሊስ የተጠርጣሪዎቹን አያያዝ በህጉ መሰረት እንዲይዝ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

ኢትዮ ኤፍ ኤም የኢትዮጵያዊያን
ነሀሴ 29 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *