ሜትር ታክሲዎች እና የቤት መኪኖች በወንበር ልክ መጫን እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አስታወቀ፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የኮሮና ቫይረስ መከሰትን ተከትሎ በወጣው የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍና የመጫን አቅም መመሪያ ላይ በተደረገው ማሻሻያ የህዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚሰጡ ሚኒባስ፣ የአንበሳ አውቶብስ፣ ሸገር እና ሀይገር ባሶች በወንበራቸው ልክ እንዲጭኑ መወሰኑ ይታወቃል፡፡

የቤት መኪኖችን እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት የሚሰጡ ተሸርካሪዎችን በሚመለከት ግን በማሻሻያው ላይ የተጠቀሰ ነገር ባመኖሩ ኢትዮ ኤፍ ኤም በዚሁ ጉዳይ ላይ ቢሮውን ጠይቋል፡፡

የቢሮው የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ሀላፊ አቶ አረጋዊ ማሩ እንደነገሩን የቤት መኪኖች እንዲሁም የሜትር ታክሲ አገልግሎት ሰጪዎችም በወንበር ልክ እንዲጭኑ መወሰኑን ነግረውናል፡፡

ከዚህ ቀደም የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ በሚል የቤት መኪኖች ከሹፌሩ ውጪ መጫን ከሚችሉት የሰው ቁጥር በግማሽ ቀንሰው ይጭኑ እንደነበር ይታወሳል፡፡

እንዲሁም ባለ ሶስት እና ባለ አራት እግር ባጃጅ ተሽከርካሪዎች እስከ ሹፌሩ 3 ሰው መጫን እንደሚችሉም ተነግሯል።

ቀላል ባቡር በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መመሪያ በ25 በመቶ የመጫን አቅም ብቻ አገልግሎት ሲሰጥ የነበረው አሁን ላይ ወደ 75 በመቶ ከፍ እንዲል መደረጉንም አስታውቋል።

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *