በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ሁለት ወረዳዎች ላይ በድጋሚ ግጭት ተቀሰቀሰ፡፡

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ፖሊስ ኮሚሽን ወንጀል መከላከል ዘርፍ ሀላፊ ኮማንደር ነጋ ጃራ ለኢትዮ ኤፍም ኤም እንዳሉት ከዚህ ቀደም በዞኑ ጉባ ወረዳ ላይ ችግር ሲፈጥሩ የነበሩ ፀረ ሰላም ሀይሎች አሁንም በወንበራና ቡለን ወረዳዎች ላይ የአካባቢውን ሰው ለመግደል ፣ለማፈናቀልና በማገት ለከፍተኛ ችግር ለመዳረግ እየተንቀሳቀሱ መሆኑን ነግረውናል፡፡

በሰዎች ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን ምን ያህል ነው? ያልናቸው ኮማደር ነጋ ሲመልሱ ወደ አካባቢው የፀጥታ ሀይሎች እንዲገቡ በማድረግ የኦፕሬሽን ስራ ተጀምሯል ፤ የጉዳቱን መጠንም በአካባቢው የተሰማሩት የፀጥታ ሀይሎች ከሚሰሩት የኦፕሬሽን ስራ ሪፖርት በኃላ እናሳውቃለን ብለውናል፡፡

በዞኑ የፀጥታ ስጋት መኖሩን ያረጋገጡልን ኮማንደር ነጋ ከሰሞኑ እነዚሁ ችግር ፈጣሪ ፀረ ሰላም ሀይሎች መልካን የሚባለው ቀበሌ ወንበራ ወረዳ ውስጥ ገብተው ሰዎችን አፍነው ገንዘብ ሲቀነበሉ እንደነበር ነግረውናል፡፡

በዚህ ድርጊታቸውም 30 የአካባቢውን ነሪዎች አፍነው ገንዘብ በመቀበል መልቀቃቸውንም ኮማንደሩ ለጣቢያችን አረጋግጠዋል፡፡

አሁን ደግሞ የመልካን ቀበሌ ቀጠናን በመልቀቅ ወደ ቡለን ወረዳ ኤጳር በሚባል አካባቢ ገብተው የአካባቢው ነዋሪዎች ላይ ችግር እየፈጠሩ መሆኑንና ከፍተኛ የፀጥታ ስጋት መኖሩን ነግረውን የፀጥታ ሀይሎች ወደ አካባቢው መግባታቸውን ነግረውናል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በትግስት ዘላለም
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *