በናይጄርያ በመንግስት ሆስፒታሎች የሚሰሩ ዶክተሮች አድማ መቱ።

በናይጄርያ በመንግስት ሆስፒታል የሚሰሩ ዶክተሮች የተሻለ ክፍያና ደህንነት እንዲሁም በቂ የስራ መገልገያ አቅርቦትን በመሻት ነው አድማውን የመቱት፡፡

ሀገሪቷ የኮሮና ወረርሽኝን ለመግታት የሞት ሽረት ትግል እያደረገች ባለችበት በዚህ ወቅት በብሄራዊ የዶክተሮች ማህበር አድማ በሀገሪቱ በስራ ላይ ካሉ 42 ሺህ ዶክተሮች ሶስት እጁ ተሳትፈዋል ተብሏል፡፡

የዶክተሮች ማህበር መሪ አሊዩ ሶኮምባ ለቢቢሲ እንደተናገሩት የኮቪድ 19 ኬዞችን የሚከታተሉ ዶክተሮች ጭምር በአድማው ተሳትፈዋል፡፡

መንግስት ፍላጎታችንን ሳያሟላ አድማውን አናቆምም ሲሉ ዝተዋል፡፡

ዶክተሮቹ የህይወት ኢንሹራንስ፣ በአገልግሎት ወቅት ለሚከሰት ሞት የሚሰጥ ጥቅም ለሁሉም ጤና ሰራኞች እንዲሰጥ የጠየቁ ሲሆን የሚያረካ ደሞዝና አበልም ይፈልጋሉ፡፡

ማህበሩ እንዳለው ኮሮና ናይጄርያ ከገባ አንስቶ 14 ዶክተሮች በኮቪድ 19 ተጠቅተው ህይወታቸው አልፏል፡፡

ወረርሽኙ ከገባ አንስቶ ክፍያና በኮቪድ የተጠቁ በሽተኞችን በሚያክሙበት ወቅት ራሳችንን መጠበቂያ ቁሳቁስ የለንም ሲሉ ያላቸውን ተቃውሞና ብስጭት ሲገልፁ ከረመዋል፡፡

በሰኔ ለሳምንት የቆየ አድማ በዶክተሮች ተደርጎ የነበረ ቢሆንም ኮሮናን የሚያክሙት ግን አድማውን አልተሳተፉም ነበር፡፡

እስካሁን ናይጄርያ ከ 55 ሺህ በላይ ዜጎቿ በኮሮና ተጠቅተውባታል፡፡

ውድ አድማጮቻችን እና ተከታዮቻችን የኢትዮ ኤፍ ኤም ስርጭቶችን፣ዜናዎችን እና ሌሎች ዝግጅቶችን ለመከታተል የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ። https://t.me/ethiofm107dot8

በሔኖክ አስራት
ጷግሜ 2 ቀን 2012 ዓ.ም

FacebooktwitterredditpinterestlinkedinmailFacebooktwitterredditpinterestlinkedinmail

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *